የብዙ አሕዛብ መንግሥታት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው አገር እንዲመለሱ ይረዱአቸዋል፤ አሕዛብ እንደ ባሪያዎች ሆነው የእስራኤልን ሕዝብ ያገለግላሉ፤ ቀድሞ እስራኤልን ማርከው የነበሩ አሁን ደግሞ በእስራኤል እጅ ይማረካሉ፤ ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ቀድሞ ይጨቊኑአቸው የነበሩትን ሁሉ የመግዛት ሥልጣን ይኖራቸዋል።
ዘኍል 31:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ከወንድ ጋር ያልተገናኙትን ልጃገረዶቹን በሕይወት እንዲኖሩ አድርጋችሁ ለራሳችሁ አስቀሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ወንድ ያላወቁትን ልጃገረዶች ሁሉ ለራሳችሁ አስቀሯቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድን በመኝታ የማያውቁትን ሴቶች ልጆችን ሁሉ ግን ለራሳችሁ በሕይወት አቆዩዋቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድን የማያውቁትን ሴቶች ልጆችን ሁሉ ግን አድኑአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድን የማያውቁትን ሴቶች ልጆችን ሁሉ ግን ለራሳችሁ አድኑአቸው። |
የብዙ አሕዛብ መንግሥታት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው አገር እንዲመለሱ ይረዱአቸዋል፤ አሕዛብ እንደ ባሪያዎች ሆነው የእስራኤልን ሕዝብ ያገለግላሉ፤ ቀድሞ እስራኤልን ማርከው የነበሩ አሁን ደግሞ በእስራኤል እጅ ይማረካሉ፤ ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ቀድሞ ይጨቊኑአቸው የነበሩትን ሁሉ የመግዛት ሥልጣን ይኖራቸዋል።
ከእናንተ መካከል ሰው የገደለ ወይም ሬሳ የነካ ሁሉ ለሰባት ቀን ከሰፈር ውጪ ይቈይ፤ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሳችሁንና የማረካችኋቸውን ሴቶች አንጹ።
ሆኖም ሴቶችንና ሕፃናት ልጆችን፥ እንስሶችንና በከተማይቱ ውስጥ ያለውን ንብረት ሁሉ ለራስህ ማርከህ ትወስዳለህ፤ የጠላቶችህ ንብረት የሆነውን ሁሉ ልትጠቀምበት ትችላለህ፤ እግዚአብሔር አምላክህ እርሱን ለአንተ አሳልፎ ሰጥቶሃል።