ዘኍል 30:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባትዋ ስለ ጉዳዩ ሰምቶ ስእለትዋን እንዳትፈጽም የሚቃወማት ከሆነ ግን ስእለትዋን የመፈጸም ግዴታ አይኖርባትም፤ ስእለትዋን ለመፈጸም ያልቻለችው አባትዋ ስለ ከለከላት በመሆኑ እግዚአብሔር ይቅርታ ያደርግላታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቷ ይህንኑ ሰምቶ ከከለከላት ግን የትኛውም ስእለቷ ወይም ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችበት መሐላ አይያዝባትም፤ የከለከላት አባቷ ስለ ሆነ እግዚአብሔር ነጻ ያደርጋታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባትዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ ስእለትዋ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላዋ አይጸኑም፤ አባትዋ ከልክሎአታልና ጌታ ይቅር ይላታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቷ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ ስእለቷ፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላዋ አይጸኑም፤ አባቷ ከልክሎአታልና እግዚአብሔር ይቅር ይላታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባትዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ ስእለትዋ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላዋ አይጸኑም፤ አባትዋ ከልክሎአታልና እግዚአብሔር ይቅር ይላታል። |
ባልዋ ስለ ጉዳዩ ሰምቶ ከከለከላት ግን የመፈጸም ግዴታ የለባትም፤ ስእለትዋን ለመፈጸም ያልቻለችው ባልዋ ስለ ከለከላት በመሆኑ እግዚአብሔር ይቅርታ ያደርግላታል።