ዘኍል 30:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባል ያገባች ሴት ስእለት ብትሳል ወይም ከአንድ ነገር ለመከልከል በመሐላ ቃል ብትገባ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከባሏ ጋራ የምትኖር ሴት ብትሳል ወይም አንድ ነገር ለማድረግ በመሐላ ራሷን ግዴታ ውስጥ ብታስገባና መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴትም በባልዋ ቤት ሳለች ብትሳል፥ ወይም ራስዋን በመሐላ ብታስር፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴትም በባልዋ ቤት ሳለች ብትሳል፥ ወይም ራስዋን በመሐላ ብታስር፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴትም በባልዋ ቤት ሳለች ብትሳል፥ ወይም ራስዋን በመሐላ ብታስር፥ |
አንድ ሰው ለእግዚአብሔር አንድ ነገር ለመስጠት ቢሳል ወይም ከአንድ ነገር ራሱን ለመከልከል በመሐላ ቃል ቢገባ፥ አደርጋለሁ ያለውን ሁሉ መፈጸም አለበት እንጂ የሰጠውን የተስፋ ቃል ማስቀረት አይገባውም።
ባልዋ የሞተባት ሴት ወይም ከባልዋ የተፋታች ሴት ማንኛቸውንም ስእለት ሆነ ወይም ከአንድ ነገር ለመከልከል የገባችውን ቃል መፈጸም አለባት።
ሕልቃናም “ጥሩ ነው፤ መልካም መስሎ የታየሽን አድርጊ፤ ጡት እስክታስጥይውም ድረስ በቤት መቈየት ትችያለሽ፤ እግዚአብሔር የሰጠሽን የተስፋ ቃል ይፈጽምልሽ” ሲል መለሰላት፤ ስለዚህም ሐና በቤት ተቀምጣ ልጇን ታሳድግ ጀመር።