ዘኍል 3:50 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእስራኤላውያን በኲሮች በመቅደሱ ሚዛን መሠረት ገንዘቡን አንድ ሺህ ሦስት መቶ ሥልሳ አምስት ሰቅል ብር ወሰደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእስራኤላውያን በኵሮች ላይ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ልክ አንድ ሺሕ ሦስት መቶ ስድሳ ዐምስት ሰቅል ሰበሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእስራኤል ልጆች በኵራት አንድ ሺህ ሦስት መቶ ስልሳ አምስት ሰቅል እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ገንዘቡን ወሰደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእስራኤል ልጆች በኵሮች ገንዘቡን ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ዲድርክም እንደ መቅደሱ ዲድርክም ሚዛን ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእስራኤል ልጆች በኵሮች ገንዘቡን ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ሰቅል እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ወሰደ። |
ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።
እርሱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን አንዴ በማያዳግም ሁኔታ የራሱን ደም ይዞ ገባ እንጂ የፍየሎችንና የወይፈኖችን ደም ይዞ አልገባም፤ በዚህም ዐይነት የዘለዓለም ቤዛን አስገኘልን።
ክርስቶስም ራሱ ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ሳለ ጽድቅ ለሌለን ለእኛ በኃጢአታችን ምክንያት በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ መከራን በመቀበል ሞቶአል፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።