ዘኍል 3:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነርሱም ኀላፊነት በድንኳኑ ተራዳዎችና በመወርወሪያዎቻቸው፥ በምሰሶቹና ምሰሶቹ በሚቆሙባቸው እግሮች፥ እንዲሁም በሌሎች የመገልገያ ዕቃዎች ላይ ሲሆን፥ በአጠቃላይ እነዚህን ነገሮች በሚመለከት ሥራ ኀላፊነቱ የእነርሱ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሜራሪያውያንም የማደሪያውን ድንኳን ሳንቃዎች፣ መወርወሪያዎች፣ ምሰሶዎች፣ ምሰሶዎቹ የሚቆሙባቸውን እግሮች፣ የማደሪያ ዕቃዎችን ሁሉና ከነዚሁ ጋራ ተያይዞ አገልግሎት የሚሰጠውን ሁሉ ለመጠበቅ ተሹመው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሜራሪም ልጆች የሚጠብቁት የማደሪያውን ሳንቆች፥ መቀርቀሪያዎቹንም፥ ምሶሶቹንም፥ እግሮቹንም፥ ዕቃዎቹንም ሁሉ መገልገያውንም ሁሉ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሜራሪም ልጆች የሚጠብቁት የድንኳኑ ምሰሶዎች፥ ኩላቦች፥ መወርወሪያዎችም፥ ተራዳዎችም፥ እግሮቹም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሜራሪም ልጆች የሚጠብቁት የማደሪያው ሳንቆች፥ መወርወሪያዎችም፥ ተራዳዎችም፥ እግሮቹም፥ ዕቃውም ሁሉ፥ |
ለመጋረጃውም አምስት ምሰሶዎችን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው፤ ኩላቦቻቸውም ከወርቅ የተሠሩ ይሁኑ፤ ለእነዚህ ምሰሶዎች ከነሐስ የተሠሩ አምስት እግሮች አብጅላቸው።
መጋረጃዎቹን የሚያያይዙ አራት ምሰሶዎችንም ከግራር እንጨት ሠርተው በወርቅ ለበጡአቸው፤ ኩላቦቻቸውንም ከወርቅ ሠሩ፤ ምሰሶዎቹ የሚቆሙባቸውን አራት እግሮችንም ከብር ሠሩ፤
ከዚህ በኋላ የሚከተሉትን ዕቃዎች ሁሉ ወደ ሙሴ አመጡአቸው፤ ድንኳኑንና የመገልገያ ዕቃዎቹን ሁሉ እነርሱም፦ ኩላቦቹ፥ ተራዳዎቹ መወርወሪያዎቹ፥ ምሰሶዎቹና የሚቆሙባቸው እግሮች፥
ለሜራሪያውያን አራት ሠረገሎችንና ስምንት በሬዎችን ሰጠ። የእነርሱም አገልግሎት የሚከናወነው የአሮን ልጅ በሆነው በኢታማር ኀላፊነት ነበር።