Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 3:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 የሜ​ራ​ሪም ልጆች የሚ​ጠ​ብ​ቁት የድ​ን​ኳኑ ምሰ​ሶ​ዎች፥ ኩላ​ቦች፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችም፥ ተራ​ዳ​ዎ​ችም፥ እግ​ሮ​ቹም፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ሜራሪያውያንም የማደሪያውን ድንኳን ሳንቃዎች፣ መወርወሪያዎች፣ ምሰሶዎች፣ ምሰሶዎቹ የሚቆሙባቸውን እግሮች፣ የማደሪያ ዕቃዎችን ሁሉና ከነዚሁ ጋራ ተያይዞ አገልግሎት የሚሰጠውን ሁሉ ለመጠበቅ ተሹመው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 የሜራሪም ልጆች የሚጠብቁት የማደሪያውን ሳንቆች፥ መቀርቀሪያዎቹንም፥ ምሶሶቹንም፥ እግሮቹንም፥ ዕቃዎቹንም ሁሉ መገልገያውንም ሁሉ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 የእነርሱም ኀላፊነት በድንኳኑ ተራዳዎችና በመወርወሪያዎቻቸው፥ በምሰሶቹና ምሰሶቹ በሚቆሙባቸው እግሮች፥ እንዲሁም በሌሎች የመገልገያ ዕቃዎች ላይ ሲሆን፥ በአጠቃላይ እነዚህን ነገሮች በሚመለከት ሥራ ኀላፊነቱ የእነርሱ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 የሜራሪም ልጆች የሚጠብቁት የማደሪያው ሳንቆች፥ መወርወሪያዎችም፥ ተራዳዎችም፥ እግሮቹም፥ ዕቃውም ሁሉ፥

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 3:36
14 Referencias Cruzadas  

ለመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም አም​ስት ምሰ​ሶ​ዎች ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አድ​ርግ፤ በወ​ር​ቅም ለብ​ጣ​ቸው፤ ኩላ​ቦ​ቻ​ቸ​ውም ከወ​ርቅ የተ​ሠሩ ይሁኑ፤ አም​ስ​ትም የናስ እግ​ሮች አድ​ር​ግ​ላ​ቸው።


በወ​ርቅ በተ​ለ​በ​ጡት፥ ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨ​ትም በተ​ሠ​ሩት በአ​ራቱ ምሰ​ሶ​ዎች ላይ ስቀ​ለው፤ ኩላ​ቦ​ቻ​ቸ​ውም ከወ​ርቅ፥ አራ​ቱም እግ​ሮ​ቻ​ቸው ከብር የተ​ሠሩ ይሁኑ።


ከካ​ህ​ኑም ከአ​ሮን ልጅ ከኢ​ታ​ምር እጅ በታች ላሉት ለሜ​ራሪ ልጆች እንደ አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው መጠን አራት ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ስም​ንት በሬ​ዎ​ችን ሰጣ​ቸው።


ድን​ኳ​ኑ​ንም፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ው​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ወደ ሙሴ አመጡ፤ መያ​ዣ​ዎ​ቹን፥ ሳን​ቆ​ቹን፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹን፥ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹን፥ እግ​ሮ​ቹ​ንም፤


ከማ​ይ​ነ​ቅ​ዝም ዕን​ጨት አራት ምሰ​ሶ​ዎች አደ​ረ​ጉ​ለት፤በወ​ር​ቅም ለበ​ጡ​አ​ቸው፤ ኵላ​ቦ​ቻ​ቸ​ውም የወ​ርቅ ነበሩ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም አራት የብር እግ​ሮች አደ​ረጉ።


የማ​ደ​ሪ​ያ​ውን ካስ​ማ​ዎች፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ካስ​ማ​ዎች፥ አው​ታ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም፤


ድን​ኳ​ኑ​ንም፥ አደ​ባ​ባ​ዩ​ንም፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ው​ንም፥ መያ​ዣ​ዎ​ቹ​ንም፥ ሳን​ቆ​ቹ​ንም፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ንና እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን፤


የሜ​ራ​ሪም ወገ​ኖች አባ​ቶች ቤት አለቃ የአ​ቢ​ኪያ ልጅ ሱራ​ሔል ነበረ፤ በድ​ን​ኳኑ አጠ​ገብ በሰ​ሜን በኩል ይሰ​ፍ​ራሉ።


ዕቃ​ውም ሁሉ፥ ማገ​ል​ገ​ያ​ውም ሁሉ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም የሚ​ቆሙ የአ​ደ​ባ​ባይ ምሰ​ሶ​ዎች፥ እግ​ሮ​ቹም፥ ካስ​ማ​ዎ​ቹም፥ አው​ታ​ሮ​ቹም ይሆ​ናሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios