ዘኍል 28:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዐሥራ አምስተኛው ቀን በዓል ነው፤ ለሰባት ቀኖች መበላት ያለበት እርሾ ያልነካው ቂጣ ብቻ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚሁ ወር በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን በዓል ይሆናል፤ እስከ ሰባትም ቀን ድረስ ቂጣ ብሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም ወር በዓሥራ አምስተኛው ቀን በዓል ይሆናል፤ ሰባት ቀን እርሾ ያልነካው ቂጣ ይበላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህም ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን በዓል ይሆናል፤ ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን በዓል ይሆናል ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ። |
ከግብጽ በወጣችሁበት በአቢብ ወር፥ እኔ ባዘዝኳችሁ አኳኋን የቂጣን በዓል አክብሩ፤ ይህ በዓል በሚከበርባቸው በሰባቱ ቀኖች ውስጥ እርሾ የነካው እንጀራ አትብሉ፤ ለእኔ ልትሰግዱ በምትመጡበት ጊዜ መባ ሳትይዙ አትምጡ።
“ከግብጽ የወጣችሁት በአቢብ ወር ስለ ሆነ የቂጣን በዓል በመጠበቅ በየዓመቱ አክብሩ፤ እንዳዘዝኳችሁ በአቢብ ወር እስከ ሰባት ቀን ቂጣ ብሉ።