ዘኍል 28:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የጌታ የፋሲካ በዓል የሚከበረው የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ፋሲካ በዓል ይከበራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዓሥራ አራተኛው ቀን የጌታ ፋሲካ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዐሥራ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጀመሪያው ወር ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው። |
ከግብጽ በወጣችሁበት በአቢብ ወር፥ እኔ ባዘዝኳችሁ አኳኋን የቂጣን በዓል አክብሩ፤ ይህ በዓል በሚከበርባቸው በሰባቱ ቀኖች ውስጥ እርሾ የነካው እንጀራ አትብሉ፤ ለእኔ ልትሰግዱ በምትመጡበት ጊዜ መባ ሳትይዙ አትምጡ።
“ከግብጽ የወጣችሁት በአቢብ ወር ስለ ሆነ የቂጣን በዓል በመጠበቅ በየዓመቱ አክብሩ፤ እንዳዘዝኳችሁ በአቢብ ወር እስከ ሰባት ቀን ቂጣ ብሉ።