ዘኍል 26:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአሴር ነገድ ተወላጆች ዪምና፥ የሱዋ፥ በሪዓ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሴር ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በዪምና በኩል፣ የዪምናውያን ጐሣ፣ በየሱዊ በኩል፣ የየሱዋውያን ጐሣ፣ በበሪዓ በኩል፣ የበሪዓውያን ጐሣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየወገናቸው የአሴር ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከዪምና የዪምናውያን ወገን፥ ከየሱዋ የየሱዋውያን ወገን፥ ከበሪዓ የበሪዓውያን ወገን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበዓሌም ልጆች አዴርና ኖሐማን፤ ከአዴር የአዴራውያን ወገን፥ ከኖሐማን የኖሐማናውያን ወገን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሴር ልጆች በየወገናቸው፤ ከዪምና የዪምናውያን ወገን፥ ከየሱዋ የየሱዋውያን ወገን፥ ከበሪዓ የበሪዓውያን ወገን። |
አሴር አራት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ይምና፥ ይሽዋ፥ ይሽዊና በሪዓ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እንዲሁም ሤራሕ ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ልጅ ወለደ።
የአሴር ልጆች፥ በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቊጥር ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤