ዘኍል 26:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የስምዖን ነገድ ተወላጆች፦ ነሙኤል፥ ያሚንና፥ ያኪን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የስምዖን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በነሙኤል በኩል፣ የነሙኤላውያን ጐሣ፤ በያሚን በኩል፣ የያሚናውያን ጐሣ፤ በያኪን በኩል፣ የያኪናውያን ጐሣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየወገናቸው የስምዖን ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከነሙኤል የነሙኤላውያን ወገን፥ ከያሚን የያሚናውያን ወገን፥ ከያኪን የያኪናውያን ወገን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የስምዖንም ልጆች በየወገናቸው፤ ከናሙሄል የናሙሄላውያን ወገን፥ ከኢያሚን የኢያሚናውያን ልጆች ወገን፥ ከያክን የያክናውያን ልጆች ወገን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የስምዖን ልጆች በየወገናቸው ከነሙኤል የነሙኤላውያን ወገን፥ ከያሚን የያሚናውያን ወገን፥ ከያኪን የያኪናውያን ወገን፥ ከዛራ የዛራውያን ወገን፥ |
ሑራም ከነሐስ የተሠሩትን ሁለት ምሰሶዎች በቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ፊት ለፊት አቆማቸው፤ ከቤተ መቅደሱ መግቢያ በር በስተ ደቡብ በኩል የቆመው ምሰሶ “ያኪን” ተብሎ ተጠራ፤ በስተ ሰሜን በኩል የቆመው ምሰሶ ደግሞ ቦዔዝ ተባለ።
የያዕቆብ በኲር ልጅ ሮቤል፥ ሐኖክ፥ ፋሉ፥ ሔጽሮንና ካርሚ የሚባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የሮቤል ነገድ አባቶች ናቸው።
ስምዖን ከከነዓናዊት ሴት የተወለደውን ሻኡልን ጨምሮ ይሙኤል፥ ያሚን፥ ኦሃድ ያኪንና፥ ጾሓር የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የስምዖን ነገድ አባቶች ናቸው።
ከስምዖን ነገድ በየትውልዳቸው በየወገናቸውና በየቤተሰባቸው፥ እንደየስማቸው ቊጥር ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆነው ወደ ጦርነት ለመውጣት የሚችል ወንድ ሁሉ በየራሳቸው የተቈጠሩት፥