ዘኍል 24:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ቄናውያን መለስ ብሎ የሚከተለውን የትንቢት ቃል ተናገረ፦ “መኖሪያህ አስተማማኝ ቢመስልና፥ ጎጆህም በተራራው ቋጥኝ ውስጥ ቢሆን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቄናውያንንም አይቶ ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤ “መኖሪያህ አስተማማኝ ነው፤ ጐጆህም በዐለት ውስጥ ተሠርቷል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቄናውያንንም አይቶ ምሳሌውን ይምስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “ማደሪያህ የጸና ነው፥ ጎጆህም በዐለት ላይ ተሠርቶአል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቄኔዎናውያንንም አይቶ በምሳሌ ይናገር ጀመር፤ እንዲህም አለ፦ “ማደሪያህ የጸናች ናት፤ ጎጆህም በአንባ ላይ ተሠርቶአል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቄናውያንምም አይቶ ምሳሌውን ይምስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ ማደሪያህ የጸና ነው፥ ጎጆህም በአምባ ላይ ተሠርቶአል፤ |
የሙሴ ዐማት የነበረው የቄናዊው ዘሮች ከይሁዳ ሕዝብ ጋር በመሆን የተምር ዛፎች ከሞሉባት ከኢያሪኮ ከተማ ተነሥተው፥ በይሁዳ ካለችው ከዐራድ በስተደቡብ ወዳለው ደረቅ ምድር ተጓዙ፤ እዚያም በዐማሌቃውያን መካከል ተቀመጡ።
“እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ ቸርነት ስላደረጋችሁላቸው እናንተን ከአማሌቃውያን ጋር እንዳላጠፋ ከዐማሌቃውያን ተለይታችሁ ሂዱ” ብሎ ሳኦል ለቄናውያን ነገራቸው። እነርሱም ከዐማሌቃውያን ተለይተው ሄዱ።