ዘኍል 23:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከግብጽ ምድር ያወጣቸው እግዚአብሔር እርሱ ለእነርሱ እንደ ጎሽ ቀንድ ይዋጋላቸዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከግብጽ አወጣቸው፤ ብርታታቸውም እንደ ጐሽ ብርታት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግብጽ ያወጣቸው እግዚአብሔር፥ ለእነርሱ እንደ ጎሽ ቀንድ ያለ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ከግብፅ ያወጣው እርሱ ጕልበቱ አንድ ቀንድ እንዳለው ክብር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ከግብፅ አውጥቶአቸዋል፤ ጕልበቱ አንድ ቀንድ እንዳለው ነው። |
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከመቅደሱ በሚገለጥበት ጊዜ እጅግ ያስፈራል፤ እርሱ ለሕዝቡ ብርታትንና ኀይልን ይሰጣል። እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
የኤዶም ሕዝብ እንደ ጐሽ፥ እንደ ኰርማና እንደ ወይፈን ይወድቃሉ፤ ነገር ግን ከሌሎች ጋር አብረው ይሞታሉ፤ ሀገሪቱም በደማቸው ትነከራለች፤ ምድሪቱም በስባቸው ትዳብራለች።
በዓማው ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ በፐቶር ከተማ ይኖር ወደነበረው ወደ ቢዖር ልጅ ወደ በለዓም ይጠሩት ዘንድ መልእክተኞች እንዲህ ብሎ ላከበት፤ “ከግብጽ የወጣ አንድ ሕዝብ ምድሪቱን ሁሉ ሸፍኖአታል፤ እነርሱም በአቅራቢያችን ሰፍረዋል፤
ከግብጽ ያወጣቸው እግዚአብሔር ለእነርሱ እንደ ጐሽ ይዋጋላቸዋል፤ ጠላቶቻቸው የሆኑትን ሕዝቦች ይቦጫጭቅላቸዋል፤ አጥንቶቻቸውን ያደቃል፤ ቀስቶቻቸውንም ይሰባብራል።
የዮሴፍ ግርማ እንደ ኰርማ አስፈሪ ነው፤ ቀንዶቹም እንደ ጐሽ ቀንዶች ጠንካሮች ናቸው፤ በእነርሱም ሕዝቦችን ይወጋል፤ እስከ ምድር ዳርቻም ያባርራል፤ የኤፍሬም ዐሥር ሺሆች የምናሴም ሺሆች እንደዚያው ናቸው።”
ግብጽን ለቃችሁ በወጣችሁ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ቀይ ባሕርን በፊታችሁ እንዴት እንዳደረቀ ሰምተናል፤ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ የነበሩትን ሁለቱን የአሞራውያን ነገሥታት ሲሖንንና ዖግን እንዴት እንደ ገደላችሁም ሰምተናል።