ዘኍል 22:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በለዓምም “ያም ሆነ ይህ አሁን መጥቼ የለምን? ታዲያ አሁንስ ቢሆን በራሴ ምን ኀይል አለኝ? እኔ ልናገር የምችለው እግዚአብሔር የሚነግረኝን ብቻ ነው” ሲል መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በለዓምም፣ “ይኸው አሁን መጥቻለሁ፤ ግን እንዲያው ማንኛውንም ነገር መናገር እችላለሁን? እኔ መናገር የሚገባኝ እግዚአብሔር በአፌ ያስቀመጠውን ብቻ ነው” ብሎ መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በለዓምም ባላቅን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ወደ አንተ መጥቼአለሁ፤ በውኑ እኔ አሁን አንዳችን ነገር ለመናገር እችላለሁን? እግዚአብሔር በአፌ የሚያድርገውን ቃል እርሱን እናገራለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በለዓምም ባላቅን፥ “እነሆ፥ ወደ አንተ መጥቼአለሁ፤ አሁን አንዳችን ነገር ለመናገር እችላለሁን? እግዚአብሔር በአፌ የሚያደርገውን ቃል እርሱን እናገራለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በለዓምም ባላቅን፦ እነሆ፥ ወደ አንተ መጥቼአለሁ፤ በውኑ አሁን አንዳችን ነገር እናገር ዘንድ እችላለሁን? እግዚአብሔር በአፌ የሚያድርገውን ቃል እርሱን እናገራለሁ አለው። |
የሐሰተኞች ነቢያትን ምልክቶችና፥ የሟርተኞችን ጥንቈላ ከንቱ አደርጋቸዋለሁ። የጥበበኞችን ዕውቀት እገለብጣለሁ፤ ዕውቀታቸውንም ወደ ሞኝነት እለውጠዋለሁ፤
በመጨረሻ የሚሆነውን ነገር ከመጀመሪያው ጀምሬ ተናግሬአለሁ፤ ወደፊት ምን እንደሚሆን ከጥንት ጀምሬ ገልጬአለሁ፤ ዓላማዬ የጸና ይሆናል፤ የምፈቅደውንም አደርጋለሁ።
እስኪ ከሆነልሽ ከሕፃንነትሽ ጊዜ ጀምሮ ስትጠቀሚባቸው የኖርሽውን ያፍዝ አደንግዝ ድግምትና የጥንቈላ መተቶችን አስቀምጪ፤ ምንአልባት ጥቂት ይረዳሽ ይሆናል፤ ወይም ጠላቶችሽን ልታስፈራሪባቸው ትችያለሽ፤
በለዓም ግን ለመልእክተኞቹ እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፤ “ባላቅ በቤተ መንግሥቱ የሚገኘውን ብርና ወርቅ ሁሉ ቢሰጠኝም በትንሽ ወይም በትልቅ ነገር የአምላኬን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መተላለፍ አይቻለኝም፤
በለዓምም “እዚሁ ዕደሩና ነገ ጧት እግዚአብሔር የሚነግረኝን ሁሉ እነግራችኋለሁ” አላቸው፤ በዚህ ዐይነት የሞአባውያን መሪዎች ከበለዓም ጋር ቈዩ።
‘ባላቅ በቤተ መንግሥቱ ያለውን ብርና ወርቅ ሁሉ ቢሰጠኝ እንኳ በራሴ ፈቃድ ደግ ወይም ክፉ ነገር አደርግ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል መተላለፍ አልችልም፤ የምናገረው እግዚአብሔር እንድናገር የነገረኝን ነገር ብቻ ነው’ ብዬ ነግሬአቸው አልነበረምን?”