ዘኍል 22:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ወደ በለዓም መጣና “እነዚህ ሰዎች ወደ አንተ የመጡት ይዘውህ ሊሄዱ ከሆነ ተነሥተህ አብረሃቸው ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ አድርግ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያች ሌሊት እግዚአብሔር ወደ በለዓም መጥቶ፣ “እነዚህ ሰዎች የመጡት እንድትሄድላቸው እስከ ሆነ ድረስ ዐብረሃቸው ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ አድርግ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ወደ በለዓም በሌሊት መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ሰዎቹ ሊጠሩህ መጥተው እንደሆነ፥ ተነሣ ከእነርሱም ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የምነግርህን ቃል ብቻ ታደርጋለህ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ወደ በለዓም በሌሊት መጥቶ፥ “ሰዎቹ ይጠሩህ ዘንድ መጥተው እንደ ሆነ፥ ተነሣ ከእነርሱ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የምነግርህን ቃል ታደርጋለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ወደ በለዓም በሌሊት መጥቶ፦ ሰዎቹ ይጠሩህ ዘንድ መጥተው እንደ ሆነ፥ ተነሣ ከእነርሱም ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የምነግርህን ቃል ብቻ ታደርጋለህ አለው። |
በእኔ ላይ ስለ መቈጣትህና ስለ ልብህ ትዕቢት ሁሉ ሰምቼአለሁ፤ ስለዚህ አሁን በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህም ልጓም አግብቼ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”
እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፦ “ ‘ገና ልጅ ነኝ’ አትበል፤ የምትሄደው እኔ ወደምልክህ ቦታ ነው፤ የምትናገረውም እኔ የማዝህን ሁሉ ነው፤
ነገር ግን እግዚአብሔር የሚነግረኝ ሌላ ነገር ካለ ከእርሱ እረዳ ዘንድ እስቲ እናንተም እንደ ፊተኞቹ መልእክተኞች ሌሊቱን እዚሁ አሳልፉ።”
መልአኩ ግን “ከእነዚህ ሰዎች ጋር መሄዱን ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ ተናገር” አለው፤ በዚህ ዐይነት በለዓም ከባላቅ ባለሥልጣኖች ጋር ሄደ።
‘ባላቅ በቤተ መንግሥቱ ያለውን ብርና ወርቅ ሁሉ ቢሰጠኝ እንኳ በራሴ ፈቃድ ደግ ወይም ክፉ ነገር አደርግ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል መተላለፍ አልችልም፤ የምናገረው እግዚአብሔር እንድናገር የነገረኝን ነገር ብቻ ነው’ ብዬ ነግሬአቸው አልነበረምን?”