ዘኍል 21:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እስራኤላውያን ዖግን፥ ልጆቹን፥ ሕዝቡን ሁሉ አንድም ሳያስቀሩ ፈጅተው ምድሩን ወረሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም እስራኤላውያን ዐግን ከልጆቹና ከመላው ሰራዊቱ ጋራ አንድም ሳይቀሩ ሁሉንም አጠፏቸው፤ ምድሩንም ወረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእርሱም አንድ ሰው በሕይወት እንዳይተርፍ አድርገው እርሱንና ልጆቹን ሕዝቡንም ሁሉ ገደሉ፤ ምድሩንም ወረሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱንና ልጆቹን፥ ሕዝቡን ሁሉ አንድ ሰው ሳያመልጥ መቱ፤ ምድሩንም ወረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱንና ልጆቹን ሕዝቡንም ሁሉ መቱ ሰውም አልቀረለትም፤ ምድሩንም ወረሱ። |
ሖራውያንም በኤዶም ይኖሩ ነበር፤ ነገር ግን የዔሳው ዘሮች ሖራውያንን ነቃቅለው በማባረር በእነርሱ ቦታ ሰፍረውበት ነበር፤ ይኸውም እስራኤላውያን ዘግየት ብለው እግዚአብሔር በሰጣቸው ምድር ላይ እንዳደረጉት ዐይነት መሆኑ ነው።]
እነዚህንም ያወጀው በዮርዳኖስ ማዶ በቤትፔዖር ሸለቆ ፊት ለፊት የአሞራውያን ንጉሥ በነበረው በሐሴቦን በነገሠውና ሙሴና እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ ተዋግተው ባሸነፉት በሲሖን ምድር ነው።
በዚያን ጊዜ እነርሱ የእርሱን ምድርና እንዲሁም በዮርዳኖስ ምሥራቅ የምትገኘውን ባሳንን ይገዛ የነበረውን የሌላውን አሞራዊ ንጉሥ የዖግን ምድር ወረሱ።
ከራፋይማውያን ተራፊ የነበረውን በአስታሮትና በኤድራይ የነገሠውን የባሳንን ንጉሥ የዖግን መንግሥት ሁሉ ይጨምራል። ሙሴም እነዚህን ድል አድርጎ አስወጣቸው።
እግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ግብጻውያን፥ አሞራውያን፥ ዐሞናውያን፥ ፍልስጥኤማውያን፥ ሲዶናውያን፥ ዐማሌቃውያንና ማዖናውያን ከዚህ በፊት ጨቊነው በገዙአችሁ ጊዜ ወደ እኔ ጮኻችሁ ነበር፤ ታዲያ እኔስ ከእነርሱ ጭቈና በመታደግ አድኛችሁ አልነበረምን?