ዘኍል 16:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከእነዚህ ሕዝብ ራቅ ብላችሁ ቁሙ፤ እኔም እነርሱን በአንድ ጊዜ እደመስሳቸዋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሁሉንም በአንድ ጊዜ እንዳጠፋቸው እናንተ ከዚህ ማኅበር ተለዩ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሁሉንም በአንድ ጊዜ ስለማጠፋቸው ከዚህ ማኅበር መካከል ተለዩ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሁሉን በቅጽበት አጠፋቸው ዘንድ ከዚህ ማኅበር መካከል ፈቀቅ በሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉን በቅጽበት አጠፋቸው ዘንድ ከዚህ ማኅበር መካከል ፈቀቅ በሉ። |
ከዚህ በኋላ ሎጥ ሴቶች ልጆቹን ወዳጩአቸው ሰዎች ቤት ሄደና “ቶሎ ብላችሁ ከዚህ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህን ስፍራ ሊደመስሰው ነው” አላቸው፤ እነርሱ ግን የሚቀልድ መስሎአቸው ቸል አሉ።
ግብጻውያን ‘እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣቸው ለክፉ ነገር፥ ማለት በተራራዎች ላይ ሊገድላቸውና ፈጽሞ ሊያጠፋቸው ነው’ እያሉ መዘባበቻ እንዲያደርጉን ለምን ትፈቅዳለህ? አሁንም ከቊጣህ ወደ ምሕረት ተመለስ፤ ይህንንም ሁሉ ጥፋት በሕዝብህ ላይ አታምጣ።
እግዚአብሔርም ለሕዝቡ እንዲህ ብሎ እንዲነግረው ሙሴን አዞት ነበር፦ “እናንተ እልኸኞች ስለ ሆናችሁ ለአንድ አፍታ እንኳ አብሬአችሁ ብሄድ ፈጽሞ እደመስሳችኋለሁ፤ አሁንም ጌጣጌጦቻችሁን አስወግዱ፤ ስለ እናንተ የማደርገውንም እወስናለሁ።”
በዚያው ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አሦራውያን ሰፈር አልፎ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤ በማግስቱ በማለዳ ሰዎች በሚነቁበት ጊዜ ሁሉም ሞተው ተገኙ።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የአሮንን በትር በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት መልሰህ አኑረው፤ ዐመፀኞች የሆኑ እስራኤላውያን በእኔ ላይ ማጒረምረማቸውን ካልተዉ እንደሚሞቱ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ይቀመጥ።”