በዓል እንዲሆን እርሱ ራሱ በወሰነው ስምንተኛ ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን ወደ ቤትኤል ሄደ፤ በዚያም ለእስራኤል በወሰነላቸው መሠረት በዓል ለማክበር በመሠዊያው ላይ መሥዋዕት አቀረበ።
ዘኍል 15:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘርፎቹም እንደማስታወሻ ሆነው ስለሚያገለግሉ፥ እነርሱን በምታዩበት ጊዜ ሁሉ ትእዛዞቼን በማስታወስ ትፈጽማላችሁ፤ ከእኔም ርቃችሁ የገዛ ፈቃዳችሁንና ምኞታችሁን የምትፈጽሙ አትሆኑም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልባችሁ የተመኘውን፣ ዐይናችሁ ያየውን ሁሉ ተከትላችሁ እንዳታመነዝሩ እነዚህን ዘርፎች በማየት የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በማስታወስ እንድትታዘዙ ማስታወሻ ይሆኗችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘርፉንም በልብሳችሁ ላይ አኑሩት እርሱንም በተመለከታችሁ ጊዜ የጌታን ትእዛዝ ሁሉ ታስታውሳላችሁ ታደርጉታላችሁም፥ ምኞታችሁንም በመከተል ያመነዘራችሁባትን የልባችሁንና የዐይኖቻችሁን ፈቃድ የማትከተሉ ትሆናላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም በዘርፉ ይሁንላችሁ፤ ትመለከቱታላችሁም፤ የእግዚአብሔርንም ትእዛዛት ታስባላችሁ፤ ታደርጉአቸውማላችሁ፤ እነርሱን በመከተል ያመነዘራችሁባትን የሕሊናችሁንና የዐይኖቻችሁን ፈቃድ አትከተሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርንም ትእዛዝ ሁሉ ታስቡና ታደርጉ ዘንድ፥ እርስዋን በመከተል ያመነዘራችሁባትን የልባችሁንና የዓይኖቻችሁን ፈቃድ እንዳትከተሉ፥ |
በዓል እንዲሆን እርሱ ራሱ በወሰነው ስምንተኛ ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን ወደ ቤትኤል ሄደ፤ በዚያም ለእስራኤል በወሰነላቸው መሠረት በዓል ለማክበር በመሠዊያው ላይ መሥዋዕት አቀረበ።
ይህም በዓል በእጃችሁ እንደ ታሰረ ምልክትና በግንባራችሁ እንዳለ ማስታወሻ ይሆንላችኋል፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ ስላወጣችሁም የእግዚአብሔር ሕግ ዘወትር ከአንደበታችሁ ሳይለይ በቃላችሁ እንድትደግሙትና እንድታጠኑት ያስታውሳችኋል።
ወጣት ሆይ! ወጣትነት እጅግ ግሩም ስለ ሆነ በወጣትነትህ ዘመን ደስ ይበልህ፤ በልብህም ሐሤት አድርግ፤ ዐይንህ የሚያየውንና ልብህ የሚመኘውን ሁሉ ፈጽም፤ ሆኖም ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።
ከሞት ያመለጣችሁት እናንተ ተማርካችሁ በሄዳችሁበት ሕዝቦች መካከል ታስታውሱኛላችሁ፤ የምታስታውሱኝም ከእኔ በራቀው ሥርዓተ አልባ በሆነው ክፉ ልባችሁና ሥርዓተ አልባ በሆነው ዐይናችሁ ጣዖቶችን በመመልከት ስላሳዘናችሁኝ ነው። በርኩስ ድርጊቶቻችሁም ላደረጋችሁት ክፉ ነገር ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።
ልጆቼ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲያ እናታችሁ ሚስቴ ስላልሆነችና እኔም ባልዋ ስላልሆንኩ የዝሙት አመለካከትዋንና አመንዝራነትዋን እንድታስወግድ ውቀስዋት።
እንደዚህ ያለው ሰው የዚህን ርግማን ቃላት ሰምቶ ምንም እንኳ በራሴ መንገድ ብቀጥል እኔ እድናለሁ ብሎ በልቡ ቢያስብ በደጎችና በክፉዎች ሰዎች ላይ ጥፋትን ያመጣል።
ስለዚህ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ እርግጠኞች ሁኑ፤ ምንም ዐይነት የተቀረጸ ምስል እንዳትሠሩ፤ የነገራችሁንም ትእዛዝ ፈጽሙ።
እናንተ ከዳተኞች! ዓለምን የሚወድ የእግዚአብሔር ጠላት መሆኑን አታውቁምን? እንግዲህ ዓለምን የሚወድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት መሆኑ ነው።