ታዲያ ትእዛዜን የናቅኸው ስለምንድን ነው? ይህንንስ ክፉ ነገር ለምን አደረግህ? ኦርዮን በጦር ሜዳ አስገደልከው፤ ንጹሑን ሰው ዐሞናውያን እንዲገድሉት አደረግህ፤ ሚስቱንም ወሰድክ!
ዘኍል 15:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሚደርስበት እግዚአብሔር የተናገረውን ችላ ስላለና ከትእዛዞቹም አንዱን ሆን ብሎ ስለ ጣሰ ነው፤ ስለዚህ ያ ሰው ፈጽሞ ይጥፋ፤ ኀላፊነቱ የራሱ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ናቀ፣ ትእዛዞቹንም ስለ ጣሰ ያ ሰው በርግጥ ተለይቶ መጥፋት አለበት፤ ጥፋቱ የራሱ ነው።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታን ቃል ስለ ናቀ፥ ትእዛዙንም ስላፈረሰ፥ ያ ሰው ፈጽሞ ይጥፋ፤ በደሉ በራሱ ላይ ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን ቃል ስለናቀ፥ ትእዛዙንም ስለ ሰበረ፥ ያ ሰው ፈጽሞ ይጥፋ፤ ኀጢአቱ በራሱ ላይ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ናቀ፥ ትእዛዙንም ስለ ሰበረ፥ ያ ሰው ፈጽሞ ይጥፋ፤ ኃጢአቱ በራሱ ላይ ነው። |
ታዲያ ትእዛዜን የናቅኸው ስለምንድን ነው? ይህንንስ ክፉ ነገር ለምን አደረግህ? ኦርዮን በጦር ሜዳ አስገደልከው፤ ንጹሑን ሰው ዐሞናውያን እንዲገድሉት አደረግህ፤ ሚስቱንም ወሰድክ!
ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ ቃል ይህ ነው፦ “እናንተ ማስጠንቀቂያን ንቃችሁ ይደግፈናል ብላችሁ በተማመናችሁበት በግፍና በማታለል ላይ እምነታችሁን ጥላችኋል።
ሁላችንም እንደ በጎች ባዝነን ነበር፤ ሁላችንም ወደ ራሳችን መንገድ ሄደን ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
ሞት የሚገባው ኃጢአት ለሚሠራ ሰው ብቻ ነው፤ ልጅ ስለ አባቱ ኃጢአት አይቀጣም፤ አባትም ስለ ልጁ ኃጢአት አይቀጣም፤ ደግ ሰው በደግነቱ መልካም ዋጋውን ያገኛል፤ ክፉ ሰውም በክፋቱ ይቀጣል።
ከሕዝብዋ ባዶ የሆነችው ምድር ውድማ ሆና ሰንበቶችን ታከብራለች፤ እነርሱም ሥርዓቴን ስላልተቀበሉና ሕጌን ስላላከበሩ፥ በኃጢአታቸው ምክንያት ቅጣቱን በሙሉ ይቀበላሉ።
ንጹሕ የሆነ እና ወደ ሩቅ አገር ያልሄደ ማንኛውም ሰው የፋሲካን በዓል በወቅቱ ባያከብር ከሕዝቤ ይለይ፤ መባውን በተወሰነው ጊዜ ባለማቅረቡ፥ ስለ ኃጢአቱ ተገቢውን ቅጣት ይቀበላል።
ዳኛውን ወይም አምላክህን እግዚአብሔርን በማገልገል ላይ ያለውን ካህን ባለመታዘዝ የሚዳፈር ሰው ቢኖር በሞት ይቀጣ። በዚህም ዐይነት እንደዚህ ያለውን ክፉ ነገር ሁሉ ከእስራኤል ታስወግዳለህ።
የጽድቅን መንገድ ካወቁ በኋላ ከተሰጣቸው ቅዱስ ትእዛዝ ወደ ኋላ ከሚመለሱ ይልቅ የጽድቅን መንገድ ሳያውቁ ቀርተው ቢሆን ኖሮ በተሻላቸው ነበር።