ዘኍል 15:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ምናልባት እናንተ ሆን ብላችሁ ሳይሆን ባለማወቅ እግዚአብሔር ለሙሴ ከሰጠው ትእዛዞች መካከል አንዱን ሳትጠብቁ ብትቀሩ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘እንግዲህ ካለማወቅ የተነሣ እግዚአብሔር ለሙሴ ከሰጣቸው ትእዛዞች አንዱን ሳትፈጽሙ ብትቀሩ፣ ይህም ማለት መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ነገር ግን ስሕተት ባለማወቅ ብትፈጽሙ፥ ጌታም ለሙሴ ያዘዛቸውን እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ባታደርጉ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ብትበድሉም፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ያዘዛቸውን እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ባታደርጉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብትስቱም፥ እግዚአብሔርም ለሙሴ ያዘዛቸውን እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ባታደርጉ፥ |
“ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ይህ ነው፦ ማንም ሰው ተሳስቶ ኃጢአት ቢሠራ ወይም ባለማወቅ ከእግዚአብሔር ትእዛዞች አንዱን ቢተላለፍ ከዚህ የሚከተለውን ሥርዓት ይጠብቅ፦
“ኃጢአት የሠራውና ባለማወቅም እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸው ትእዛዞች አንዱን የተላለፈውና በደለኛ የሆነው ሰው ከተራው ሕዝብ ወገን ከሆነ፥
ካህኑም በዚህ ዐይነት ስለዚያ ሰው ኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕትን ያቀርባል፤ ያም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል፤ የቀረው ዱቄት የእህል መባ በሚቀርብበት ዐይነት ለካህኑ ይሁን።”
ነገር ግን የጌታውን ፈቃድ ባለማወቅ፥ ቅጣት የሚያመጣበትን ነገር አድርጎ ቢገኝ ቅጣቱ ይቀልለታል፤ ብዙ ከተሰጠው ሰው ብዙ ይፈለግበታል፤ ብዙ ዐደራም ከተሰጠው ሰው፥ ብዙ ይጠበቅበታል።”