ለሙሴም እንዲህ ብለው ነገሩት፦ “ምድሪቱን አጥንተን በእርግጥም በማርና በወተት የበለጸገች አገር መሆንዋን ተረድተናል፤ ምድሪቱም የምታፈራው ፍሬ ዐይነት ይህ ነው፤
ዘኍል 14:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሕዝቡም እንዲህ አሉ፦ “መርምረን ያጠናናት ምድር እጅግ ውብ የሆነች ምድር ናት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመላው የእስራኤል ማኅበርም እንዲህ አሉ፤ “ዞረን ያየናትና የሰለልናት ምድር እጅግ ሲበዛ መልካም ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲህ ብለው ተናገሩ፦ “ዞረን የሰለልናት ምድር እጅግ መልካም የሆነች ናት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ “የሰለልናት ምድር እጅግ በጣም መልካም ናት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ፦ ዞረን የሰለልናት ምድር እጅግ መልካም ናት። |
ለሙሴም እንዲህ ብለው ነገሩት፦ “ምድሪቱን አጥንተን በእርግጥም በማርና በወተት የበለጸገች አገር መሆንዋን ተረድተናል፤ ምድሪቱም የምታፈራው ፍሬ ዐይነት ይህ ነው፤
ካሌብ ግን በሙሴ ፊት ሕዝቡን ጸጥ በማሰኘት “እነርሱን ድል ለመንሣት የሚያስችል በቂ ኀይል ስለ አለን አገሪቱን አሁኑኑ ሄደን እንያዛት አለ።”
እነርሱም እንዲህ አሉአቸው፦ “እንግዲህ ኑ! በላዪሽ ላይ አደጋ እንጣል! ምድሪቱ በጣም ጥሩ መሆንዋን አይተናል፤ እዚህ ያለ ሥራ ቦዝናችሁ አትቀመጡ፤ ይልቅስ በፍጥነት ሄዳችሁ ያዙአት!