ዘኍል 14:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማሌቃውያንና ከነዓናውያን በሸለቆዎቹ ውስጥ ስለሚኖሩ ነገ ተመልሳችሁ በቀይ ባሕር በኩል በሚወስደው መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አማሌቃውያንና ከነዓናውያን በሸለቆው የሚኖሩ ስለ ሆነ በነገው ዕለት ተመልሳችሁ በቀይ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳው ሂዱ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አማሌቃውያንና ከነዓናውያን በሸለቆው ውስጥ ስለ ተቀመጡ ነገ ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር በኩል በሚወስደው መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐማሌቅና ከነዓናዊውም በሸለቆ ውስጥ ተቀምጠዋል፤ እናንተ ግን ነገ ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አማሌቅና ከነዓናዊውም በሸለቆው ውስጥ ተቀምጦአል፤ በነጋው ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ። |
ዐማሌቃውያን በኔጌብ ምድር የሚኖሩ ሲሆን፥ ሒታውያን፥ ኢያቡሳውያንና አሞራውያን በተራራማው አገር፥ ከነዓናውያን ደግሞ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርና በሜዲቴራኒያን በባሕር ዳር ይኖራሉ።”