ዘኍል 13:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎቹ ምድሪቱን ለአርባ ቀኖች ካጠኑ በኋላ ተመለሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድሪቱንም ዐሥሠው ከአርባ ቀን በኋላ ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድሪቱንም ሰልለው ከአርባ ቀን በኋላ ተመለሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድሪቱንም ሰልለው ከአርባ ቀን በኋላ ከዚያ ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድሪቱንም ሰልለው ከአርባ ቀን በኋላ ተመለሱ። |
ሙሴም ምንም ሳይበላና ሳይጠጣ ከእግዚአብሔር ጋር አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቈየ፤ ጌታም በጽላቶቹ ላይ የቃል ኪዳን ቃላት የሆኑትን ዐሥሩን ትእዛዞች ጻፈ።
በፋራን ምድረ በዳ በቃዴስ ወደነበሩት ወደ ሙሴና አሮን ወደ መላውም የእስራኤል ማኅበር መጡ፤ እነርሱም ያዩትን ነገር ሁሉ አስረዱ፤ ያመጡትንም ፍሬ አሳዩአቸው፤