በኋላም እግዚአብሔር በዖዝያ ላይ የቆዳ በሽታ አሳደረበት፤ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ይህ በሽታ ስላልለቀቀው ከሥራው ሁሉ ተገልሎ በተለየ ቤት ውስጥ ለብቻው ይኖር ነበር፤ በዚህም ጊዜ መንግሥቱን ሲመራ የቈየው ልጁ ኢዮአታም ነበር።
ዘኍል 12:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደመናው ከድንኳኑ ላይ በተነሣ፤ ጊዜ ማርያም ለምጻም ሆነች፤ ለምጹም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ፤ አሮን ወደ ማርያም በተመለከተ ጊዜ ለምጻም ሆና አያት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደመናው ከድንኳኑ ላይ በተነሣ ጊዜ፣ እነሆ፤ ማርያም በለምጽ ተመታች፤ እንደ በረዶም ነጣች። አሮንም ወደ እርሷ ዘወር ሲል ለምጽ ወርሷት አየ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደመናውም ከድንኳኑ በተነሣ ጊዜ እነሆ፥ ማርያም በለምጽ ደዌ ተይዛ እንደ በረዶ ነጭ ሆና ነበር፤ አሮንም ወደ ማርያም ዘወር አለ፥ እነሆም፥ በለምጽ ደዌ ተይዛ ተመለከተ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደመናውም ከድንኳኑ ተነሣ፤ እነሆም፥ ማርያም ለምጻም ሆነች፤ እንደ በረዶም ነጭ ሆነች፤ አሮንም ማርያምን ተመለከተ፤ እነሆም፥ ለምጻም ሆና ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደመናውም ከድንኳኑ ተነሣ፤ እነሆም፥ ማርያም ለምጻም ሆነች፥ እንደ አመዳይም ነጭ ሆነች፤ አሮንም ማርያምን ተመለከተ፥ እነሆም፥ ለምጻም ሆና ነበር። |
በኋላም እግዚአብሔር በዖዝያ ላይ የቆዳ በሽታ አሳደረበት፤ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ይህ በሽታ ስላልለቀቀው ከሥራው ሁሉ ተገልሎ በተለየ ቤት ውስጥ ለብቻው ይኖር ነበር፤ በዚህም ጊዜ መንግሥቱን ሲመራ የቈየው ልጁ ኢዮአታም ነበር።
ከዚህም የተነሣ እነሆ፥ የንዕማን የቆዳ በሽታ ወደ አንተ ይተላለፋል፤ አንተና ዘሮችህ ለዘለዓለም ከዚያ በሽታ አትነጹም!” አለው። ግያዝም ወጥቶ ሲሄድ፥ ያ የቆዳ በሽታ ስለ ተጋባበት ገላው እንደ በረዶ ነጭ ሆነ።
ሰውነታቸው የቆዳ በሽታ የያዛቸው አራት ሰዎች ከሰማርያ ቅጽር በር ውጪ ነበሩ፤ እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “እስክንሞት ድረስ ስለምን በዚህ እንቈያለን?
እንደገናም እግዚአብሔር ሙሴን “እጅህን ወደ ብብትህ አስገባው” አለው፤ እርሱም እጁን ወደ ብብቱ አስገባ፤ እጁንም ከብብቱ ባወጣው ጊዜ እንደ በረዶ ነጭ ሆነ።
“የሥጋ ደዌ በሽታ ያለበትን፥ ወይም ከሰውነቱ ፈሳሽ የሚወጣውንና ሬሳ በመንካት የረከሰውን ሰው ሁሉ ከሰፈር ያወጡ ዘንድ እስራኤላውያንን እዘዝ፤
ከዚህ በኋላ በግራው በኩል ያሉትንም እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለተከታዮቹ መላእክት ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ!