መሪዎቹ መኖሪያቸውን በኢየሩሳሌም አደረጉ፤ ከሌላውም ሕዝብ መካከል ከየዐሥር ቤተሰብ አንዱ እጅ ቅድስት በሆነችው በኢየሩሳሌም ከተማ እንዲኖር በዕጣ ተመረጠ፤ የቀሩት ሰዎች ግን በሌሎች መንደሮችና ከተሞች ሁሉ ኑሮአቸውን መሠረቱ፤
ነህምያ 7:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሩሳሌም ታላቅና ሰፊ ከተማ ሆና ነበር፤ ነገር ግን የሚኖርባት ሕዝብ ቊጥር አነስተኛ ነበር፤ ገና ብዙ ቤቶችም አልተሠሩባትም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተማዪቱ ታላቅና ሰፊ ነበረች፤ የሚኖርባት ሕዝብ ግን ጥቂት ሲሆን፣ ቤቶች ገና አልተሠሩባትም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተማይቱ ሰፊና ታላቅ ነበረች፤ በውስጧ የነበሩ ሕዝብ ግን ጥቂቶች ነበሩ፤ ቤቶችም አልተሠሩም ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተማዪቱም ሰፊና ታላቅ ነበረች፤ በውስጥዋ የነበሩ ሕዝብ ግን ጥቂቶች ነበሩ፤ ቤቶቹም ገና አልተሠሩም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተማይቱም ሰፊና ታላቅ ነበረች፥ በውስጥዋ የነበሩ ሕዝብ ግን ጥቂቶች ነበሩ፥ ቤቶቹም አልተሠሩም ነበር። |
መሪዎቹ መኖሪያቸውን በኢየሩሳሌም አደረጉ፤ ከሌላውም ሕዝብ መካከል ከየዐሥር ቤተሰብ አንዱ እጅ ቅድስት በሆነችው በኢየሩሳሌም ከተማ እንዲኖር በዕጣ ተመረጠ፤ የቀሩት ሰዎች ግን በሌሎች መንደሮችና ከተሞች ሁሉ ኑሮአቸውን መሠረቱ፤
ለእነርሱም የሰጠኋቸው መመሪያ የኢየሩሳሌም የቅጽር በሮች ፀሐይ እስኪሞቅ ድረስ እንዳይከፈቱ፥ ደግሞ ማታ ፀሐይ ስትጠልቅ የዘብ ጠባቂዎቹ ከመሄዳቸው በፊት የቅጽር በሮቹ በቊልፍና በመወርወሪያ አጥብቀው እንዲዘጉአቸው ነበር። እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች መካከል ሰዎችን ቀጥረው ከፊሎቹ በሥራቸው ላይ ሆነው ሌሎቹ ደግሞ በየቤታቸው ፊት ለፊት ሆነው እንዲጠብቁ አዘዝኳቸው።
እግዚአብሔርም ሕዝቡንና መሪዎቻቸው የሆኑ ባለሥልጣኖችን እንድሰበስብና የቤተሰባቸውን የትውልድ ሐረግ አመዘጋገብ እንድቈጣጠር አነሣሣኝ፤ ቀደም ባለው ጊዜ የተመለሱትንም ምርኮኞች የትውልድ ሐረግ ማስረጃ መዝገብ አገኘሁ፤ ያገኘሁትም ማስረጃ ከዚህ የሚከተለው ነበር።
ሕዝባችሁ ቀድሞ ፈራርሰው የነበሩትን ሁሉ እንደገና መልሶ በጥንቱ መሠረት ላይ ይሠራል፤ ስለዚህም እናንተ ‘ቅጽሮችን መልሶ የሚያንጽና ፈራርሰው የነበሩ ቤቶችን የሚያድስ ሕዝብ’ ተብላችሁ ትጠራላችሁ።”