ነህምያ 5:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአይሁድ ወገኖቻችን ጋር ዘራችን አንድ ነው፤ የእኛ ልጆች ከእነርሱ ልጆች የሚለዩበት ምንም ነገር የለም፤ ይሁን እንጂ የገዛ ልጆቻችንን ለባርነት አሳልፈን ለመስጠት ተገደናል፤ እንዲያውም ከሴቶች ልጆቻችን አንዳንዶቹ ባሪያዎች ሆነዋል፤ ነገር ግን እርሻችንና የወይን ተክል ቦታችን ስለ ተወሰዱ ኀይል የሌለን ሆነናል” በማለት አቤቱታ አሰሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምንም እንኳ ከአገራችን ሰዎች ጋራ በሥጋና በደም አንድ ብንሆንም፣ እንደ እነርሱ ልጆች ሁሉ የእኛም ወንዶች ልጆች ጥሩዎች ቢሆኑም፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንን ባሮች እንዲሆኑ ሰጥተናል፤ አንዳንድ ሴቶች ልጆቻችን አሁንም በባርነት ላይ ናቸው፤ ዕርሻችንና የወይን ተክል ቦታችን የሌሎች በመሆናቸው እኛ ደካሞች ሆነናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም ሥጋችን እንደ ወንድሞቻችን ሥጋ፥ ልጆቻችንም እንደ ልጆቻቸው ናቸው፤ እነሆ ወንዶች ልጆቻችንና ሴቶች ልጆቻችን ባርያዎች እንዲሆኑ ለማምጣት ተገደናል፥ አንደንድ ሴቶች ልጆቻችን አሁንም ለባርነት ተወስደዋል፤ እርሻችንና የወይን ቦታችን ለሌሎች ስለሆነ ኃይል በእጃችን የለም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ሥጋችን እንደ ወንድሞቻችን ሥጋ፥ ልጆቻችንም እንደ ልጆቻቸው ናቸው፤ እነሆም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ባሪያዎች ይሆኑ ዘንድ ሰጥተናል፤ ከሴቶችም ልጆቻችን ባሪያዎች ሆነው የሚኖሩ አሉ፤ ታላላቆችም እርሻችንንና ወይናችንን ይዘዋልና ልናድናቸው አንችልም” የሚሉ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ሥጋችን እንደ ወንድሞቻችን ሥጋ፥ ልጆቻችንም እንደ ልጆቻቸው ናቸው፥ እነሆም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ባሪያዎች ይሆኑ ዘንድ ሰጥተናል፥ ከሴቶችም ልጆቻችን ባሪያዎች ሆነው የሚኖሩ አሉ፥ ታላላቆችም እርሻችንና ወይናችንን ይዘዋልና ልናድናቸው አንችልም ይሉ ነበር። |
እርሱ የሥጋ ወንድማችን ስለ ሆነ” በእርሱ ላይ ጒዳት ከምናደርስበት ይልቅ ለእነዚህ እስማኤላውያን ነጋዴዎች ብንሸጠው ይሻላል፤ ወንድሞቹም በዚህ ሐሳብ ተስማሙ።
የነቢያት ጉባኤ አባል የነበረ ባልዋ የሞተባት አንዲት ሴት ወደ ኤልሳዕ መጥታ “ጌታዬ ሆይ! ባሌ ሞቶብኛል! እርሱም አንተ እንደምታውቀው እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበር፤ ነገር ግን እነሆ ለባሌ ገንዘብ አበድሮት የነበረ አንድ ሰው በባሌ ዕዳ ፈንታ ሁለት ወንዶች ልጆቼን ወስዶ ባሪያ አድርጎ ሊገዛቸው ፈልጎአል” አለችው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወንድ ሚስቱን ፈቶ እንደሚያባርር እኔ እናንተን ሕዝቤን ያባረርኩ ይመስላችኋልን? ይህስ ከሆነ የፍችው ደብዳቤ የት አለ? ሰው ልጆቹን ለባርነት እንደሚሸጥ እኔም እናንተን ለምርኮ አሳልፌ የሸጥኳችሁ ይመስላችኋልን? ከሆነስ ለማንኛውም አበዳሪዬ ሸጥኳችሁ? እናንተ ለምርኮ የተሰጣችሁት በኃጢአታችሁ ምክንያት ነው፤ የተሰደዳችሁትም በፈጸማችሁት በደል ነው።
ምግባችሁን ከተራበ ሰው ጋር እንድትካፈሉ፥ ማደሪያ የሌለውን ድኻ በቤታችሁ እንድትቀበሉ፥ የተራቈቱትን እንድታለብሱ፥ ከቅርብ ዘመዶቻችሁም ራሳችሁን እንዳትደብቁ አይደለምን?