ከአንተ ጋር የነበርኩበትን ኻያ ዓመት ያሳለፍኩት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ከዚህም ዐሥራ አራቱን ዓመት ያገለገልኩህ ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ለማግኘት ብዬ ነው፤ የቀሩትን ስድስት ዓመቶች ያገለገልኩህ መንጋዎችህን ለማግኘት ብዬ ነው። ይህም ሆኖ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ ለዋወጥክብኝ።
ነህምያ 4:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጠላቶቻችን መካከል የሚኖሩ አይሁድ ወደ ከተማው እየመጡ ጠላቶቻችን እኛን ለማጥቃት ያቀዱ መሆናቸውን ደጋግመው በማስጠንቀቅ ነገሩን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በአጠገባቸው የሚኖሩ አይሁድ መጥተው፣ “እናንተ የትም ቦታ ብትሆኑ፣ እኛን ማጥቃታቸው አይቀርም!” በማለት ዐሥር ጊዜ ደጋግመው ነገሩን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እያንዳንዱ ግንበኛ ሰይፉን በወገቡ ታጥቆ ይሠራ ነበር፤ ቀንደ መለከትም የሚነፋውም በአጠገቤ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአጠገባቸውም የተቀመጡት አይሁድ መጥተው፥ “ከስፍራው ሁሉ ይመጡብናል ብለው ዐሥር ጊዜ ነገሩን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአጠገባቸውም የተቀመጡት አይሁድ መጥተው፦ ከስፍራው ሁሉ ይመጡብናል ብለው አሥር ጊዜ ነገሩን። |
ከአንተ ጋር የነበርኩበትን ኻያ ዓመት ያሳለፍኩት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ከዚህም ዐሥራ አራቱን ዓመት ያገለገልኩህ ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ለማግኘት ብዬ ነው፤ የቀሩትን ስድስት ዓመቶች ያገለገልኩህ መንጋዎችህን ለማግኘት ብዬ ነው። ይህም ሆኖ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ ለዋወጥክብኝ።
ስለዚህም ከሕዝባችን መካከል ሰይፍ፥ ጦርና ቀስት የያዙ ሰዎችን በየጐሣቸው በማዘጋጀት፥ ሥራው ባልተጠናቀቀበት ቦታ ሁሉ በቅጽሩ ግንብ በስተጀርባ እንዲመሸጉ አደረግሁ።
ጥበብና ማስተዋልን በተመለከቱ ጉዳዮች ንጉሡ በሚጠይቃቸው ነገሮች በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት ከሚገኙ ጠንቋዮችና አስማተኞች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ብልጫ ያላቸው ሆነው አገኛቸው።
ከእነዚህ ሕዝብ አንዱም ወደዚያች ምድር ለመግባት በሕይወት አይኖርም፤ በግብጽ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግኋቸውን ተአምራት ሁሉ አይተዋል፤ ነገር ግን የትዕግሥቴን ብዛት ደጋግመው በመፈታተን ለእኔ መታዘዝ እምቢ አሉ።