ነህምያ 3:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱም ቀጥሎ ያለውን ክፍል የኢየሩሳሌም ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው የሑር ልጅ ረፋያ ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ የሚቀጥለውን ክፍል የኢየሩሳሌም አውራጃ እኩሌታ ገዥ የሆነው የሑር ልጅ ረፋያ መልሶ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአጠገባቸውም የኢየሩሳሌም ግዛት እኩሌታ ገዢ የሁር ልጅ ሬፋያ አደሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአጠገባቸውም የኢየሩሳሌም ግዛት እኩሌታ አለቃ የሆር ልጅ ረፋያ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአጠገባቸውም የኢየሩሳሌም ግዛት እኩሌታ አለቃ የሆር ልጅ ረፋያ አደሰ። |
የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዢ የነበረው የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ እስከ ዳዊት መቃብር (ከዳዊት መቃብር ትይዩ ጀምሮ)፥ እስከ ኩሬ፤ እስከ ጀግኖች ሰፈር ድረስ ያለውን ክፍል ሠራ።
በቅጽሩ ሥራ ተካፋዮች የነበሩት ሌዋውያን ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፦ የባኒ ልጅ ረሑም ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ። የቀዒላ ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው ሐሻብያ ወረዳውን በመወከል ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ።