እንዲህም አላቸው፦ “እናንተ ሌዋውያን! ራሳችሁን መቀደስና የቀድሞ አባቶቻችሁን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤተ መቀደስ ማንጻት አለባችሁ፤ ቤተ መቅደሱን የሚያረክስ ነገር ሁሉ ከቤተ መቅደሱ ማስወገድ ይኖርባችኋል።
ነህምያ 13:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፍሎቹም በሕጉ መሠረት በሥርዓት እንዲነጹና የቤተ መቅደሱም ንዋያተ ቅድሳት፥ የእህል መባውና ዕጣኑ ወደዚያ ተመልሰው እንዲገቡ ትእዛዝ ሰጠሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፍሎቹንም እንዲያነጹ ትእዛዝ ሰጠሁ፤ ከዚያም የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃዎች፣ የእህሉን ቍርባንና ዕጣኑን ጭምር መልሼ አስገባሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጓዳዎቹንም እንዲያነጹ አዘዝሁ፥ የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃዎች የእህሉንም ቁርባን ዕጣኑንም መልሼ በዚያ አገባሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕቃ ቤቶቹንም እንዲያነጹ አዘዝሁ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃዎች፥ የእህሉንም ቍርባን፥ ዕጣኑንም መልሼ በዚያ አገባሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጓዳዎቹንም እንዲያነጹ አዘዝሁ፥ የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃዎች የእህሉንም ቍርባን ዕጣኑንም መልሼ በዚያ አገባሁ። |
እንዲህም አላቸው፦ “እናንተ ሌዋውያን! ራሳችሁን መቀደስና የቀድሞ አባቶቻችሁን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤተ መቀደስ ማንጻት አለባችሁ፤ ቤተ መቅደሱን የሚያረክስ ነገር ሁሉ ከቤተ መቅደሱ ማስወገድ ይኖርባችኋል።
ከሰበሰብነው መከር የመጀመሪያውን እህል ዱቄት ወስደን በቤተ መቅደስ ለሚያገለግለው ካህን እንሰጣለን፤ ሌላውንም የወይን ጠጅ፥ የወይራ ዘይትና የመሳሰለውንም ፍራ ፍሬ ሁሉ የመጀመሪያውን መባ አድርገን እናቀርባለን። ከእርሻ መንደሮቻችን ግብር ለሚሰበስቡት ሌዋውያንም ምድራችን ከምታበቅለው የእህል መከር ዐሥራት እያወጣን እንሰጣለን።
የይሁዳም ሕዝብ ተደስቶ የነበረው እነርሱ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት መፈጸም የሚገባውን ደንብና የማንጻት ሥርዓት በማከናወናቸው ነበር፥ የቤተ መቅደሱ መዘምራንና የቤተ መቅደሱ ዘብ ጠባቂዎችም ዳዊትና ልጁ ሰሎሞን በመደቡት ሥርዓት መሠረት የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት ፈጸሙ።
በውጪው አደባባይ በስተ ሰሜን በኩል ከውስጠኛው የቅጽር በር ጋር የተያያዘ ሌላም ተጨማሪ ክፍል ነበር፤ እርሱም ከአደባባዩ ፊት ለፊት ወደሚገኘው ወደ መግቢያው ክፍል የሚያስገባ ሌላ በር ነበረው፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ የእንስሶች ሥጋ የሚታጠበውም በዚያ ነበር።