ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው።
ነህምያ 12:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤተ መቅደሱ ቅጽር በር አጠገብ የተሠሩትን የዕቃ ግምጃ ቤቶች የሚጠብቁ ዘበኞችም ማታንያ፥ ባቅቡቅያ፥ አብድዩ፥ መሹላም፥ ጣልሞንና ዓቁብ ተብለው የሚጠሩት ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቅጥሩ በሮች አጠገብ ያሉትን ዕቃ ቤቶች የሚጠብቁት ዘቦች ደግሞ መታንያ፣ በቅቡቅያ፣ አብድዩ፣ ሜሱላም፣ ጤልሞንና ዓቁብ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማታንያ፥ ባቅቡቅያ፥ አብድዩ፥ ምሹላም፥ ጣልሞን፥ ዓቁብ በበሮቹ አጠገብ የሚገኙትን ዕቃ ቤቶች የሚጠብቁ በር ጠባቂዎች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መታንያ፥ በቅቡቅያ፥ አብድያ፥ ሜሱላም፥ ጤልሞን፥ ዓቁብ በበሮች አጠገብ የሚገኙትን ዕቃ ቤቶች ለመጠበቅ በረኞች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መታንያ፥ በቅቡቅያ፥ አብድዩ፥ ሜሱላም፥ ጤልሞን፥ ዓቁብ በበሮች አጠገብ የሚገኙትን ዕቃ ቤቶች ለመጠበቅ በረኞች ነበሩ። |
ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው።
እንዲሁም እግዚአብሔር የሚመለክበትን ድንኳንና ቤተ መቅደሱን የመንከባከብ ኀላፊነት የእነርሱ ነበር፤ በተጨማሪም በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሚፈጸመው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት ዘመዶቻቸውን የአሮን ዘሮች የሆኑ ካህናትን ይረዱ ነበር።
የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎች በየቤተሰቡ በቡድን ተከፍለው ነበር፤ እነርሱም ልክ እንደ ሌሎቹ ሌዋውያን በቤተ መቅደሱ ውስጥ አገልግሎት ነበራቸው፤
በየቀኑ በምሥራቅ በኩል ስድስት፥ በሰሜን አራት፥ በደቡብ አራት ዘብ ጠባቂዎች ይመደባሉ፤ እንዲሁም በየቀኑ አራት ዘብ ጠባቂዎች የዕቃ ግምጃ ቤቶቹን ለመጠበቅ ሲመደቡ፥ ከእነርሱ ሁለቱ አንዱን የዕቃ ግምጃ ቤት፥ ሁለቱ ደግሞ ሌላውን ይጠብቁ ነበር።
አባቱ ዳዊት የደነገጋቸውን መመሪያዎች በመከተልም የካህናቱንና ካህናቱን በሥራና መዝሙር በመዘመር የሚረዱትን ሌዋውያን የየዕለቱን የሥራ መደብ አቀናበረ፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ባዘዘው መሠረት የቤተ መቅደሱ ዘበኞች በእያንዳንዱ ቅጽር በር የዕለት ሥራቸውን እንዲያከናውኑ አከፋፍሎ መደበ።