ሚክያስ 3:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔን ግን እግዚአብሔር በመንፈሱና በኀይሉ ሞልቶኛል፤ የእስራኤል ሕዝብ በደላቸውና ኃጢአታቸው ምን እንደ ሆነ አስታውቃቸው ዘንድ በግልጽ ትክክለኛ ፍርድን ለመስጠት ብርታትን ሰጥቶኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ግን፣ ለያዕቆብ በደሉን፣ ለእስራኤልም ኀጢአቱን እነግር ዘንድ፣ ኀይልን በእግዚአብሔር መንፈስ፣ ፍትሕና ብርታትም ተሞልቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ግን በደሉን ለያዕቆብ፥ ኃጢአቱንም ለእስራኤል እንድነግር በጌታ መንፈስ ኃይልን፥ ፍትህና ብርታት ተሞልቻለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን በደሉን ለያዕቆብ፥ ኃጢአቱንም ለእስራኤል እነግር ዘንድ በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልንና ፍርድን ብርታትንም ተሞልቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ግን በደሉን ለያዕቆብ፥ ኃጢአቱንም ለእስራኤል እነግር ዘንድ በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልንና ፍርድን ብርታትንም ተሞልቻለሁ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ድምፅህን ሳትቈጥብ ጩኽ! ድምፅህ እንደ እምቢልታ ከፍ ይበል! ለሕዝቤ ለእስራኤል ዐመፃቸውንና ኃጢአታቸውን ንገራቸው።
ለተጨቈኑት መልካም ዜናን አበሥር ዘንድ፥ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩት ነጻነትን፥ ለታሰሩት መፈታትን ለማወጅ እግዚአብሔር ቀብቶ ስለ ላከኝ፥ የጌታ እግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው።
ኤርምያስ ሆይ! እነሆ አድምጠኝ! በዚህ ምድር የሚኖሩ ሁሉ፥ ይህም ማለት የይሁዳ ነገሥታት ባለሥልጣኖች፥ ካህናቱና ሕዝቡም ሳይቀሩ በአንተ ላይ በጠላትነት ይነሡብሃል፤ ይሁን እንጂ እነርሱን ለመቋቋም የሚያስችልህን ኀይልና ብርታት እሰጥሃለሁ፤ እንደ ተመሸገች ከተማ፥ እንደ ብረት ምሰሶና ከነሐስ እንደ ተሠራ ግንብ ጠንካራ አደርግሃለሁ፤ እኔ ከአንተ ጋር ሆኜ በመጠበቅ ስለምከላከልልህ እነርሱ ከቶ ሊያሸንፉህ አይችሉም፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
ነገር ግን “ከእንግዲህ እግዚአብሔርን አላስታውስም፤ በስሙም አልናገርም” በምልበት ጊዜ፥ ከእርሱ የተሰጠኝ የትንቢት ቃል በውስጤ እንደ እሳት ይነዳል፤ በውስጤ ሰውሬ ልይዘው ብሞክርም፤ አፍኜ ላስቀረው አይቻለኝም።
ጌታ ሆይ! አንተ በእነርሱ ላይ ያለህ ቊጣ በእኔም ውስጥ ይነዳል። ከቶም ልታገሠው አልችልም።” እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ “ቊጣዬን በመንገድ ላይ በሚገኙ ሕፃናትና በተሰበሰቡ ወጣቶች ላይ አፍስሰው፤ ባልና ሚስት በአንድነት ይወሰዳሉ፤ በዕድሜ ለገፉ ሽማግሌዎች እንኳ ምሕረት አይደረግላቸውም።”
የእናንተ ነቢያት ሐሰተኛና አታላይ ራእይ አይተውላችኋል፤ ሐሰተኛና አሳሳች ትንቢት ተናገሩ እንጂ፥ ዕድል ፈንታችሁን ለመለወጥ በደላችሁን አላጋለጡም።
“የሰው ልጅ ሆይ! በእነዚህ ሰዎች ላይ ትፈርድባቸዋለህን? ትፈርድባቸዋለህን? እንግዲያውስ አባቶቻቸው ያደረጉትን አጸያፊ ነገር እንዲያውቁ አድርጋቸው።
“የሰው ልጅ ሆይ! በነፍሰ ገዳዮች የተሞላችውን ከተማ ልትፈርድባት ተዘጋጅተሃልን? እንግዲያውስ የፈጸመቻቸውን አጸያፊ ነገሮች ሁሉ ገልጠህ አሳያት።
እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! በኦሆላና በኦሆሊባ ላይ ፍርድ ለመስጠት ተዘጋጅተሃልን? ያደረጉትን አጸያፊ ነገር ግለጥላቸው፤
ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ለእስራኤል ሕዝብ ስለ ቤተ መቅደሱ አሠራር ንገራቸው፤ ንድፉንም ያጥኑ፤ ኃጢአት የሞላበት ሥራቸውንም በማስታወስ እንዲያፍሩ አድርጋቸው።