La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 8:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ፥ ኢየሱስ የመቶ አለቃውን “ሂድ፤ እንደ እምነትህ ይሁንልህ” አለው። አገልጋዩም በዚያኑ ሰዓት ተፈወሰ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢየሱስም መቶ አለቃውን፣ “ሂድ! እንደ እምነትህ ይሁንልህ” አለው። ብላቴናውም በዚያች ቅጽበት ተፈወሰ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢየሱስም ለመቶ አለቃው “ሂድና እንደ እምነትህ ይሁንልህ፤” አለው። ብላቴናውም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢየሱስም ለመቶ አለቃ “ሂድና እንዳመንህ ይሁንልህ፤” አለው። ብላቴናውም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢየሱስም ለመቶ አለቃ፦ ሂድና እንዳመንህ ይሁንልህ አለው። ብላቴናውም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 8:13
10 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ቀድሞ የፈቀደልህ ይህ በመሆኑ ሂድ፤ ምግብህን ተመግበህ፥ የወይን ጠጅህንም ጠጥተህ በመርካትህ ደስ ይበልህ።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ “አንቺ ሴት እምነትሽ! ትልቅ ነው፤ ስለዚህ እንደ ፍላጎትሽ ይሁንልሽ!” አላት። የሴትዮዋም ልጅ በዚያኑ ሰዓት ዳነች።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እምነታችሁ ጐደሎ ስለ ሆነ ነው፤ በእውነት እላችኋለሁ፤ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያኽል እምነት ቢኖራችሁ ይህን ተራራ ‘ከዚህ ተነሥተህ ወዲያ ሂድ!’ ብትሉት ይሄዳል፤ የሚሳናችሁም ምንም ነገር አይኖርም።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፥ ከለምጹ የዳነውን ሰው እንዲህ አለው፤ “ይህን ነገር ለማንም አትናገር፤ ነገር ግን ሄደህ መዳንህን ለካህን አሳይ፤ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ፥ ስለ መዳንህ ሙሴ ያዘዘውን መባ ለእግዚአብሔር አቅርብ” አለው።


ኢየሱስም መለስ ብሎ አያትና “አይዞሽ ልጄ ሆይ! እምነትሽ አድኖሻል” አላት። ሴትዮዋም ወዲያውኑ ዳነች።


ስለዚህ ኢየሱስ፥ “በዚህ አነጋገርሽ ጋኔኑ ከልጅሽ ወጥቶአል፤ እንግዲህ ወደ ቤትሽ ሂጂ!” አላት።


ኢየሱስም “ብትችል” ትላለህን? “ለሚያምን ሰው ሁሉ ነገር ይቻላል!” አለው።


ኢየሱስም “ወደ ቤትህ ሂድ! ልጅህ በሕይወት ይኖራል” አለው። ሰውየውም ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አምኖ ወደ ቤቱ ሄደ።