ማቴዎስ 7:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱንም የምታውቁአቸው በሥራቸው ፍሬ ነው። ከእሾኽ ቊጥቋጦ የወይን ፍሬ፥ ከኮሸሽላስ የበለስ ፍሬ ይለቀማልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ፤ ከእሾኽ ቍጥቋጦ ወይን፣ ከኵርንችትስ በለስ ይለቀማልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ፤ ከእሾህ የወይን ፍሬ፥ ከኮሸሽላስ በለስ ይለቀማልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? |
ነገር ግን “አንተ እምነት አለህ፤ እኔም መልካም ሥራ አለኝ” የሚል ቢኖር፥ “እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔም በሥራዬ እምነቴን አሳይሃለሁ” እለዋለሁ።
ወንድሞቼ ሆይ፥ የበለስ ዛፍ የወይራን ፍሬ ሊያፈራ ይችላልን? ወይስ የወይን ተክል የበለስ ፍሬ ሊያፈራ ይችላልን? እንዲሁም ከመራራ ውሃ ጣፋጭ ውሃ ሊገኝ ይችላልን?
‘ክፉ ነገርን የሚያደርጉ ክፉ ሰዎች ብቻ ናቸው’ የተባለውን ጥንታዊ አነጋገር ታውቃለህ፤ ስለዚህም እኔ በአንተ ላይ ጒዳት ላደርስብህ አልፈልግም።