ዳዊትም ወደ እነርሱ ቀርቦ እንዲህ አላቸው፤ “ወደዚህ የመጣችሁት በወዳጅነት ልትረዱኝ ከሆነ መልካም ነው፤ በደስታ እቀበላችኋለሁ፤ ከእኛም ጋር ሁኑ! እኔ ምንም ሳላደርጋችሁ ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ ከሆነ ግን የቀድሞ አባቶቻችን አምላክ ተመልክቶ ይፍረደው።”
ማቴዎስ 5:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰዎች መካከል ዕርቅና ሰላምን የሚያደርጉ፥ የእግዚአብሔር ልጆች ስለሚባሉ የተባረኩ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፤የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና። |
ዳዊትም ወደ እነርሱ ቀርቦ እንዲህ አላቸው፤ “ወደዚህ የመጣችሁት በወዳጅነት ልትረዱኝ ከሆነ መልካም ነው፤ በደስታ እቀበላችኋለሁ፤ ከእኛም ጋር ሁኑ! እኔ ምንም ሳላደርጋችሁ ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ ከሆነ ግን የቀድሞ አባቶቻችን አምላክ ተመልክቶ ይፍረደው።”
ይህን ብታደርጉ፥ በሰማይ ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆናላችሁ። እርሱ ለክፉዎችና ለደጎች ፀሐዩን ያወጣል፤ እንዲሁም ለጻድቃንና ለግፈኞች ዝናቡን ያዘንባል።
እናንተ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ! መልካም ነገርም አድርጉላቸው፤ ‘ብድራችን ይመለስልናል’ ብላችሁ ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ይህን ብታደርጉ ዋጋችሁ ትልቅ ይሆናል፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጆችም ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለውለታ ቢሶችና ለክፉዎች እንኳ ሳይቀር ቸር ነው።
በማግስቱም ሁለት እስራኤላውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አገኘና ሊገላግላቸው በመፈለግ ‘እናንተ ሰዎች፥ እናንተ ወንድማማች ናችሁ፤ ስለምን ትጣላላችሁ?’ አላቸው።
በተረፈውስ ወንድሞቼ ሆይ! ደኅና ሁኑ! አኗኗራችሁን አስተካክሉ፤ ምክሬን ተከተሉ፤ እርስ በእርሳችሁ ተስማሙ፤ በሰላምም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
እግዚአብሔር ሰዎችን በእኛ አማካይነት ስለሚጠራ እኛ የክርስቶስ እንደራሴዎች ነን፤ ስለዚህ “ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ!” ብለን በክርስቶስ ስም እንለምናችኋለን።
እርስ በርሳችሁ ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ይቅር በሉ።