ማቴዎስ 4:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም ዲያብሎስ ኢየሱስን በጣም ከፍ ወዳለ ተራራ ላይ አውጥቶ፥ የዓለምን መንግሥታት ሁሉ ከነክብራቸው አሳየውና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገናም ዲያብሎስ ኢየሱስን እጅግ ከፍ ወዳለ ተራራ አወጣው፤ የዓለምን መንግሥታት ከነክብራቸው አሳየውና፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደገና ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፤ የዓለምን መንግሥታት ሁሉና ክብራቸውን አሳየውና፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፤ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ፦ |
ምን ያኽል ሀብታም እንደ ሆነና ምን ያኽል ልጆች እንዳሉት፥ ንጉሡም ሥልጣኑን ከፍ በማድረግና በመሾም የቱን ያኽል እንዳከበረው፥ ከሌሎቹ የመንግሥት ባለሥልጣኖች ይበልጥ የተከበረ ሰው መሆኑንም በትምክሕት ገለጠላቸው፤
ንጉሡም እንዲህ አለ፦ “ይህችን ታላቋን ባቢሎን የነገሥታት መኖሪያና ዋና ከተማ ሆና የእኔ ክብርና ግርማ እንዲገለጥባት በሥልጣኔ የሠራኋት እኔ አይደለሁምን?”
ከዚህ በኋላ በለዓም ባላቅን “እግዚአብሔር ወደ እኔ መምጣቱን ወይም አለመምጣቱን ለማወቅ ወደዚያ ሄጄ እስክረዳ ድረስ እዚህ በሚቃጠል መሥዋዕትህ አጠገብ ቁም፤ እግዚአብሔር የሚገልጥልኝን ነገር ሁሉ እነግርሃለሁ” አለው፤ ከዚያም በኋላ ብቻውን ወደ አንድ ኮረብታ ወጣ።
ሰባተኛውም መልአክ እምቢልታውን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት የጌታ የአምላካችንና የመሲሑ ሆናለች፤ እርሱ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤” የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ።