አሁንም የአኗኗራችሁንና የሥራችሁን ሁኔታ ለውጣችሁ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይኖርባችኋል፤ ይህን ብታደርጉ በእናንተ ላይ ሊያመጣ ያቀደውን ጥፋት ይመልሰዋል።
ማቴዎስ 3:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲያውስ ንስሓ መግባታችሁን የሚያመለክት ሥራ ሥሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ለንስሓ የሚገባ ፍሬ አፍሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አፍሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤ |
አሁንም የአኗኗራችሁንና የሥራችሁን ሁኔታ ለውጣችሁ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይኖርባችኋል፤ ይህን ብታደርጉ በእናንተ ላይ ሊያመጣ ያቀደውን ጥፋት ይመልሰዋል።
የይሁዳ ሕዝብ በእነርሱ ላይ ላመጣ ያቀድኩትን ጥፋት በሚሰሙበት ጊዜ ምናልባት ከክፉ ሥራቸው ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ።”
መጥምቁ ዮሐንስ የጽድቅን መንገድ ሊያሳያችሁ ቢመጣ አላመናችሁትም፤ ኃጢአተኞችና ዘማውያን ግን አመኑት፤ ይህንንም አይታችሁ እንኳ ንስሓ ገብታችሁ አላመናችሁትም።”
ይልቁንስ ንስሓ መግባታችሁን የሚያመለክት ሥራ ሥሩ እንጂ እኛ የአብርሃም ልጆች ነን እያላችሁ በልባችሁ አትመኩ። እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እንደሚችል እነግራችኋለሁ።
ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ያሉት ሰዎች፥ ቀጥሎም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምድር ሁሉ ያሉት እንዲሁም አሕዛብ ጭምር ንስሓ ገብተው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ አስተማርኳቸው፤ ንስሓ መግባታቸውን የሚያመለክት ነገር እንዲያደርጉም አስተማርኳቸው።