ማቴዎስ 25:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሽራው በመዘግየቱ ሁሉም እንቅልፍ ተጫጭኖአቸው ተኙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሽራው በዘገየ ጊዜ፣ ሁሉም እንቅልፍ ተጫጫናቸውና ተኙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ፥ ሁሉም እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ፥ ሁሉም እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ። |
እኔ ተኝቼአለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቶአል፤ ውዴ እንዲህ እያለ በር ሲያንኳኳ ሰማሁት፤ “ውድ እኅቴ የሆንሽ ሙሽራዬ ሆይ! እንከን የሌለብሽ ርግቤ ሆይ! እባክሽ በሩን ክፈችልኝ፤ ራሴ በጠል ርሶአል ጠጒሬም በሌሊት ካፊያ ረስርሶአል።”
ምክንያቱም ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ይጠብቃል፤ እርሱም የሚናገረው የሚፈጸምበትን ቀን ነው፤ ሐሰትም የለበትም፤ ጊዜ የሚወስድ ቢመስልም ጠብቅ፤ በእርግጥ ይደርሳል፤ አይዘገይምም።
ከዚህ በኋላ ወደ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ተመልሶ በመጣ ጊዜ ተኝተው አገኛቸው፤ ስለዚህ፥ ጴጥሮስን እንዲህ አለው፦ “ከእኔ ጋር ለአንዲት ሰዓት እንኳ መንቃት አልቻላችሁምን?
ነገር ግን ያ አገልጋይ ‘ጌታዬ ቶሎ አይመጣም፤ ይዘገያል’ ብሎ በማሰብ እየበላ፥ እየጠጣ፥ እየሰከረም ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችን መምታት ይጀምራል።
ቀጥሎም ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ለሕዝቡ መናገር ጀመረ፦ “አንድ ሰው የወይን ተክል ተከለ፤ ለገበሬዎች አከራየውና ወደ ሌላ አገር ሄደ፤ ሳይመለስም ብዙ ጊዜ ቈየ።
እንግዲህ ከእንቅልፍ የምትነቁበት ሰዓት አሁን መድረሱን ዕወቁ፤ በፊት ካመንበት ጊዜ ይልቅ አሁን የምንድንበት ቀን ይበልጥ ወደ እኛ ቀርቦአል።