ማቴዎስ 24:49 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሥራ ጓደኞቹን መደብደብ ቢጀምር፥ ከሰካራሞችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተነሥቶ ሌሎች አገልጋይ ባልንጀሮቹን መምታት ቢጀምር፣ ከሰካራሞችም ጋራ ቢበላና ቢጠጣ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባልንጀሮቹን ባርያዎች መደብደብ ቢጀምር፥ ከሰካራሞችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባልንጀሮቹን ባሮች ሊመታ ቢጀምር፥ ከሰካሮችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባልንጀሮቹን ባሮች ሊመታ ቢጀምር ከሰካሮችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥ |
ቃሉን የምታከብሩ እናንተ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ “ስለ ስሜ የሚጠሉአችሁና የሚያገሉአችሁ እንዲህ ይሉአችኋል፦ ‘እናንተ ስትደሰቱ እናይ ዘንድ እስቲ እግዚአብሔር ክብሩን ይግለጥ፤’ ኀፍረት ላይ የሚወድቁት ግን እነርሱ ራሳቸው ናቸው።
ወተቱን ትጠጣላችሁ፤ ከጠጒራቸው የተሠራውንም ሱፍ ትለብሳላችሁ፤ የሰባውንም በግ ዐርዳችሁ ትበላላችሁ፤ ነገር ግን በጎችን በማሰማራት አትጠብቁም፤
እግዚአብሔር ስለ ሐሰተኞች ነቢያት እንዲህ ይላል፦ “ጥቅም የሚያገኙበት ሲሆን ‘ሰላም ይወርድላችኋል’ እያሉ ይሰብካሉ፤ ጥቅም በማያገኙበት ጊዜ ‘ጦርነት ይመጣባችኋል’ እያሉ በማወጅ ሕዝቡን ያስታሉ፤
“ነገር ግን ያ አገልጋይ ከዚያ ወጥቶ ሲሄድ ሳለ መቶ ዲናር ያበደረውን የሥራ ጓደኛውን አገኘና አንገቱን አንቆ ይዞ፥ ‘ያበደርኩህን ገንዘብ ክፈለኝ!’ አለው።
“ሰው ሁሉ አስቀድሞ የሚያቀርበው ጥሩውን የወይን ጠጅ ነው፤ ተጋባዦቹ ከጠጡ በኋላ መናኛውን ያቀርባል፤ አንተ ግን ጥሩውን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቈየህ።”
እንዲሁም ማንም እንደ ባሪያ ቢያደርጋችሁ፥ ማንም ቢበዘብዛችሁ፥ ማንም ቢጠቀምባችሁ፥ ማንም ቢንቃችሁ፥ ማንም ፊታችሁን በጥፊ ቢመታችሁ ትታገሣላችሁ።
የእነርሱ አምላክ ሆዳቸው ነው፤ አሳፋሪ የሆነ ነገር ለእነርሱ ክብራቸው ነው፤ ሐሳባቸውም የሚያተኲረው በምድራዊ ነገር ላይ ነው፤ ስለዚህ የእነርሱ መጨረሻ ጥፋት ነው።
እነዚህ ሰዎች ያለ ኀፍረት በመዳራት በአንድነት ግብዣችሁ ላይ ሲገኙ እንቅፋት ይሆኑባችኋል፤ እነርሱ የሚያስቡት ስለ ራሳቸው ብቻ ነው፤ በነፋስ እንደሚገፋ፥ ዝናብ እንደሌለው ደመና ናቸው። በፍሬ ወራት እንኳ ፍሬ እንደማይገኝበት፥ ከስሩ እንደ ተነቀለና ሁለት ጊዜ እንደ ሞተ ዛፍ ናቸው።
ቅዱሳንን እንዲዋጋና ድል እንዲነሣቸው ሥልጣን ተሰጠው፤ በነገድና በወገን፥ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች በሚናገሩና በሕዝብ ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።
በትእዛዜ መሠረት የሚቀርብልኝን መሥዋዕትና ቊርባን ለምን ታዋርዳላችሁ? ልጆችህ ለመሥዋዕት ከሚቀርበው ምርጥ የሆነውን እየወሰዱ በመብላት ይወፍሩ ዘንድ እነርሱን ከእኔ ይበልጥ የምታከብራቸው ለምንድነው?’