እርሱም “መልካም ነው፤ እናንተ ባላችሁት እስማማለሁ፤ ሆኖም ዋንጫውን የወሰደው ሰው ብቻ የእኔ ባሪያ ይሆናል፤ የቀራችሁት ግን በነጻ ልትሄዱ ትችላላችሁ” አላቸው።
ማቴዎስ 18:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ መተሳሰብ በጀመረ ጊዜ በብዙ ሺህ መክሊት የሚቈጠር ዕዳ ያለበት አንድ አገልጋይ ተይዞ መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሒሳቡን ማጣራት እንደ ጀመረም ዐሥር ሺሕ ታላንት ዕዳ ያለበትን አንድ አገልጋይ አቀረቡለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መተሳሰብ በጀመረ ጊዜ፥ አስር ሺህ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መቈጣጠርም በጀመረ ጊዜ፥ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መቍኦጣጠርም በጀመረ ጊዜ፥ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። |
እርሱም “መልካም ነው፤ እናንተ ባላችሁት እስማማለሁ፤ ሆኖም ዋንጫውን የወሰደው ሰው ብቻ የእኔ ባሪያ ይሆናል፤ የቀራችሁት ግን በነጻ ልትሄዱ ትችላላችሁ” አላቸው።
ከመቶ ሰባ ሺህ ኪሎ የሚበልጥ ወርቅ፥ ከሦስት መቶ አርባ ሺህ ኪሎ በላይ የሚሆን ብር፥ ወደ ስድስት መቶ ኻያ ሺህ ኪሎ የሚጠጋ ነሐስና ከሦስት ሚሊዮን አራት መቶ ሺህ ኪሎ በላይ የሆነ ብረት በፈቃዳቸው ለመስጠት ወሰኑ፤
“አምላኬ ሆይ፥ ኃጢአታችን ከራሳችን በላይ ስለ ሆነና በደላችንም ወደ ሰማይ ስለ ደረሰ ፊቴን ወደ አምላኬ ወደ አንተ ለማቅናት ዐፍራለሁ እፈራለሁም።
ከቊጥር በላይ የሆኑ ችግሮች ያስጨንቁኛል! በደሎቼ ስለ በዙ ማየት አልችልም፤ እነርሱም በቊጥር ከራስ ጠጒሮቼ ይበልጣሉ፤ ስለዚህ ልቤም እየከዳኝ ነው።
ጌትዮው ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው በማካፈል፥ ለአንዱ አምስት መክሊት፥ ለአንዱ ሁለት መክሊት፥ ለአንዱ ደግሞ አንድ መክሊት ሰጠና ወደ ሌላ አገር ሄደ።
አምስት መክሊት የተቀበለው አገልጋይ ወደ ጌታው መጣና አምስት መክሊት አቅርቦ ‘ጌታ ሆይ! አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ! ሌላ አምስት መክሊት አትርፌአለሁ!’ አለ።
በሰሊሆም ግንብ ተደርምሶባቸው ስለሞቱት ዐሥራ ስምንት ሰዎች ምን ታስባላችሁ? እነርሱ በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሰዎች ሁሉ የባሱ ኃጢአተኞች የነበሩ ይመስሉአችኋልን?
ሁለተኛውንም ጠርቶ፥ ‘የአንተስ ዕዳ ምን ያኽል ነው?’ አለው። እርሱም ‘መቶ ዳውላ ስንዴ ዕዳ አለብኝ’ ሲል መለሰ። መጋቢውም ‘ይኸው የፈረምከው ውል! ሰማኒያ ዳውላ ብለህ ጻፍ’ አለው።