ማቴዎስ 17:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከስድስት ቀን በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስን፥ ያዕቆብንና የያዕቆብን ወንድም ዮሐንስን ብቻ አስከትሎ፥ ለብቻው ወደ አንድ ከፍተኛ ተራራ ላይ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከስድስት ቀን በኋላ ኢየሱስ፣ ጴጥሮስንና ያዕቆብን እንዲሁም የያዕቆብን ወንድም ዮሐንስን ወደ አንድ ረዥም ተራራ ብቻቸውን ይዟቸው ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከስድስት ቀን በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስን ያዕቆብንና ወንድሙ ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን ይዞአቸው ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። |
ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ጴጥሮስ፥ ያዕቆብ፥ ዮሐንስና፥ እንድርያስ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው
ኢየሱስ ወደ ኢያኢሮስ ቤት በደረሰ ጊዜ ከጴጥሮስ፥ ከዮሐንስ፥ ከያዕቆብ፥ ከልጅትዋ አባትና እናት በቀር ሌላ ማንም ከእርሱ ጋር ወደ ውስጥ እንዲገባ አልፈቀደም።
ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኀይልና ስለ ዳግመኛ መምጣቱም በነገርናችሁ ጊዜ ራሳችን ግርማውን በዐይናችን አይተን የምንመሰክር እንጂ በሰው ተንኰል የታቀደውን ተረት ተከትለን አይደለም።