ኢየሱስና ጴጥሮስ ወደ ጀልባው በገቡ ጊዜ ነፋሱ ጸጥ አለ።
ኢየሱስና ጴጥሮስ ጀልባው ላይ እንደ ወጡ ነፋሱ ጸጥ አለ።
ወደ ጀልባዋ በወጡ ጊዜ ነፋሱ ፀጥ አለ።
ወደ ታንኳይቱም በወጡ ጊዜ ነፋሱ ተወ።
ኢየሱስ ወዲያውኑ እጁን ዘርግቶ ያዘውና፦ “አንተ እምነት የጐደለህ! ስለምን ተጠራጠርክ?” አለው።
በጀልባውም ውስጥ የነበሩት ሁሉ “በእርግጥ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ!” ብለው ለኢየሱስ ሰገዱለት።
እነርሱም በጣም ፈርተው፥ እርስ በርሳቸው “ኧረ ለመሆኑ፥ ነፋስና ባሕር እንኳ የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?” ተባባሉ።
ወደ ጀልባውም ገብቶ፥ ከእነርሱ ጋር በሆነ ጊዜ ነፋሱ ቆመ፤ ደቀ መዛሙርቱ በጣም ተደነቁ።
እነርሱም በደስታ ተቀብለው ወደ ጀልባዋ ሊያስገቡት ፈለጉ፤ ወዲያውኑ ጀልባዋ ወደሚሄዱበት ቦታ ደረሰች።