ማቴዎስ 14:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሄሮድስ ዮሐንስን አስይዞ በወህኒ ቤት አሳስሮት ነበር፤ ይህንንም ያደረገው የወንድሙ የፊልጶስ ሚስት በነበረችው በሄሮዲያዳ ምክንያት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀደም ሲል ሄሮድስ፣ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ ወህኒ አስገብቶት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሄሮድስ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ አሳስሮትና እስር ቤት አስገብቶት ነበርና፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄሮድስ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ አሳስሮት በወህኒ አኑሮት ነበርና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሄሮድስ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ አሳስሮት በወህኒ አኑሮት ነበርና፤ |
የኢየሱስ ዝና በሁሉም ዘንድ ስለ ታወቀ፥ ንጉሡ ሄሮድስ ስለ እርሱ ሰማ። አንዳንድ ሰዎች፥ “መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነሥቶአል፤ ስለዚህ ይህ ሁሉ ተአምራት በእርሱ ይደረጋል” ይሉ ነበር።
ስለዚህም የሄሮዲያዳ ልጅ ወደ ግብዣው አዳራሽ ገብታ እየጨፈረች ሄሮድስንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ተጋባዦች አስደሰተች፤ ንጉሡም ልጅትዋን፦ “የምትፈልጊውን ማንኛውንም ነገር ጠይቂኝ፤ እሰጥሻለሁ” አላት፤
በዚያን ጊዜ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መጥተው፥ “የገሊላ ሰዎች መሥዋዕት በሚያቀርቡበት ጊዜ ጲላጦስ ገደላቸው፤ ደማቸውም ከመሥዋዕታቸው ጋር አደባለቀ” ሲሉ ነገሩት።
የሮም ንጉሠ ነገሥት ጢባርዮስ በነገሠ በዐሥራ አምስተኛው ዓመት፥ ጰንጤናዊው ጲላጦስ የይሁዳ ምድር አስተዳዳሪ ነበር፤ ሄሮድስ የገሊላ አገረ ገዢ ነበር፤ እንዲሁም ወንድሙ ፊልጶስ የኢጡርያስና የጥራኮኒዶስ ገዢ፥ ሊሳኒዮስም የአቢሌኔ ገዢ ነበሩ፤
የሄሮድስ ቤት አዛዥ የነበረው የኩዛ ሚስት ዮሐና፥ ሶስናና ሌሎችም ብዙዎች ነበሩ፤ እነዚህ ሴቶች ኢየሱስንና ደቀ መዛሙርቱን በገንዘባቸው ያገለግሉ ነበር።
“በእርግጥም ሄሮድስና ጴንጤናዊ ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በዚህች ከተማ ተሰብስበው መሲሕ ባደረግኸው በቅዱሱ አገልጋይህ በኢየሱስ ላይ ተነሡ፤