እጅግ አስፈሪ የሆነ ቊጣቸው፥ እጅግ ጨካኝ የሆነ መዓታቸው፥ የተረገመ ይሁን። በእስራኤል ምድር ሁሉ እበታትናቸዋለሁ፤ በሕዝቡም መካከል እከፋፍላቸዋለሁ።
ማቴዎስ 14:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተቈረጠውንም ራስ በሳሕን አምጥተው ለልጅቱ ሰጡአት፤ እርስዋም ለእናትዋ ወስዳ ሰጠች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተቈረጠውም ራስ በሳሕን ላይ ተደርጎ ለብላቴናዪቱ ተሰጣት፤ ብላቴናዪቱም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራሱን በሳሕን መጥቶ ለልጅቱ ተሰጣት፤ እርሷም ወደ እናትዋ ወሰደችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ራሱንም በወጭት አምጥተው ለብላቴናይቱ ሰጡአት፤ ወደ እናትዋም ወሰደችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራሱንም በወጭት አምጥተው ለብላቴናይቱ ሰጡአት፥ ወደ እናትዋም ወሰደችው። |
እጅግ አስፈሪ የሆነ ቊጣቸው፥ እጅግ ጨካኝ የሆነ መዓታቸው፥ የተረገመ ይሁን። በእስራኤል ምድር ሁሉ እበታትናቸዋለሁ፤ በሕዝቡም መካከል እከፋፍላቸዋለሁ።
ስለዚህ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ ለግድያ አዘጋጃችኋለሁ፤ ገዳይም ያሳድዳችኋል፤ ደም ማፍሰስን ስላልጠላችሁ ገዳይ ያሳድዳችኋል።