ማቴዎስ 13:55 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ የአናጢው ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም የምትባል አይደለችምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብ፥ ዮሴፍ፥ ስምዖንና ይሁዳ አይደሉምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ የዐናጺው ልጅ አይደለምን? የእናቱስ ስም ማርያም አይደለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብ፣ ዮሴፍ፣ ስምዖንና ይሁዳ አይደሉምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ የጠራቢው ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብ፥ ዮሴፍ፥ ስምዖንና ይሁዳ አይደሉምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ፥ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን? |
በሕዝቦች ዘንድ በጣም ለተናቅህና ለተጠላህ፥ ለገዢዎችም አገልጋይ ለሆንክ ለአንተ፥ አዳኙ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ነገሥታት ሲያዩህ ይነሡልሃል፤ ልዑላንም ይሰግዱልሃል፤ ይህም የሚሆነው በመረጠህ በታማኙ በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ምክንያት ነው።”
በሩቅ ሆነው የሚመለከቱ፥ አንዳንድ ሴቶችም በዚያ ነበሩ። ከእነርሱም መካከል መግደላዊት ማርያም፥ የታናሹ ያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም፥ ሰሎሜም ይገኙ ነበር።
ቀጥለውም “ለመሆኑ ይህ እንጨት ጠራቢው የማርያም ልጅ አይደለምን? የያዕቆብ፥ የዮሳ የይሁዳና የስምዖን ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ እዚህ ከእኛ ጋር አይደሉምን?” እያሉ በመናቅ ሳይቀበሉት ቀሩ።
ኢየሱስ የማስተማር ሥራውን ሲጀምር፥ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያኽል ሆኖት ነበር፤ ለሕዝቡ ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ ይመስላቸው ነበር፤ ይኸውም ዮሴፍ የዔሊ ልጅ፥
እንዲህም አሉ፦ “ይህ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለምን? አባቱንና እናቱንስ እናውቃቸው የለምን? ታዲያ፥ አሁን እርሱ እንዴት ‘ከሰማይ ወረድኩ’ ይላል?”
የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና የያዕቆብ ወንድም ከሆነው ከይሁዳ፥ ለተጠራችሁት፥ በእግዚአብሔር አብ ለተወደዳችሁት፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለተጠበቃችሁት ሁሉ፥