ስለዚህም ንዕማን የእግዚአብሔር ሰው ባዘዘው መሠረት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠበ፤ ከበሽታውም ፈጽሞ ነጻ፤ ሥጋውም እንደ ትንሽ ልጅ ገላ በመታደስ ፍጹም ጤናማ ሆነ፤
ማቴዎስ 11:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ ዕውሮች ያያሉ፤ አንካሶች ቀጥ ብለው ይሄዳሉ፤ ለምጻሞች ይነጻሉ፤ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፤ ሙታን ይነሣሉ፤ ለድኾችም ወንጌል ይሰበካል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐይነ ስውራን ያያሉ፤ ዐንካሶች ይራመዳሉ፤ ለምጻሞች ይነጻሉ፤ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፤ ሙታን ይነሣሉ፤ ለድኾችም የምሥራች እየተሰበከ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕውሮች ያያሉ፤ አንካሶች ይራመዳሉ፤ ለምጻሞችም ይነጻሉ፤ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፤ ሙታን ይነሣሉ፤ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕውሮች ያያሉ፤ አንካሶችም ይሄዳሉ፤ ለምጻሞችም ይነጻሉ፤ ደንቆሮችም ይሰማሉ፤ ሙታንም ይነሣሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዕውሮች ያያሉ አንካሶችም ይሄዳሉ፥ ለምጻሞችም ይነጻሉ ደንቆሮችም ይሰማሉ፥ ሙታንም ይነሣሉ |
ስለዚህም ንዕማን የእግዚአብሔር ሰው ባዘዘው መሠረት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠበ፤ ከበሽታውም ፈጽሞ ነጻ፤ ሥጋውም እንደ ትንሽ ልጅ ገላ በመታደስ ፍጹም ጤናማ ሆነ፤
የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ በቊጣ ልብሱን ቀደደ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ “የሶርያ ንጉሥ ይህን ሰው እንደምፈውስለት አድርጎ እንዴት ይገምታል? እኔ ሰውን ከቈዳ በሽታ እፈውስ ዘንድ የማዳንና የመግደል ሥልጣን ያለኝ እግዚአብሔር መሰልኩትን? በእርግጥ ይህ አባባል ከእኔ ጋር ጠብ መፈለጉን በግልጥ ያሳያል!” አለ።
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለሰው አፍን የፈጠረለት ማነው? ድዳ ወይም ደንቆሮ፥ ዐይኑ እንዲያይ ወይም እንዳያይ የሚያደርግስ ማነው? ይህን ሁሉ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?
እነዚህን ሁሉ ነገሮች የፈጠርኩ እኔ ነኝ፤ ስለዚህ ሁሉም የእኔ ናቸው፤ እኔ የምመለከተው ልባቸው ወደ ተሰበረ፥ ትሑት መንፈስ ወዳላቸውና፥ ቃሌንም ወደሚያከብሩ ነው።
በጎቹን ይገዙና ይሸጡ ለነበሩት ሰዎች ተቀጥሬ እንዲታረዱ ለተፈረደባቸው የበጎች መንጋ እረኛ ሆንኩ፤ መንጋውንም በማሰማራበት ጊዜ ሁለት በትሮችን ወሰድኩ፤ አንደኛውን በትር “ተወዳጅ” ብዬ ጠራሁት፤ ሌላውን በትር “አንድነት” ብዬ ጠራሁት።
ኢየሱስም ሕዝቡ እየተራወጡ ሲመጡ አየ፤ ርኩሱንም መንፈስ “አንተ ድዳና ደንቆሮ መንፈስ ከልጁ እንድትወጣ ወደ እርሱም ተመልሰህ እንዳትገባ አዝሃለሁ!” ብሎ ገሠጸው።
“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ መልካም ዜናን ለድኾች እንዳበሥር ሾሞኛል፤ ለታሰሩት መፈታትን፥ ለዕውሮች ማየትን እንዳውጅና የተጨቈኑትንም ነጻ እንዳወጣ ልኮኛል፤
የአባቴን ሥራ የምሠራ ከሆንኩ ግን በእኔ እንኳ ባታምኑ በሥራዬ እመኑ፤ በዚህ ዐይነት አብ በእኔ እንደ ሆነና እኔም በአብ እንደ ሆንኩ በሚገባ ታውቃላችሁ።”
ይህ ሰው በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ “መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ካልሆነ በቀር እነዚህን አንተ የምታደርጋቸውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል ማንም የለም፤ ስለዚህ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣህ መምህር እንደ ሆንክ እናውቃለን” አለው።
እኔ ግን ከዮሐንስ ምስክርነት የበለጠ ምስክር አለኝ፤ ምስክሬም አባቴ እንድሠራው የሰጠኝ ሥራ ነው፤ ይህም የምሠራው ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራል።
“የእስራኤል ሰዎች ሆይ! ይህን ቃል አዳምጡ፤ እናንተ ራሳችሁ እንደምታውቁት የናዝሬቱ የኢየሱስ ማንነት እግዚአብሔር በእናንተ መካከል በእርሱ አማካይነት በፈጸማቸው ታላላቅ ሥራዎች፥ ተአምራትና ምልክቶች ተረጋግጦአል።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?