አሁን ግን ሴቲቱን ለባልዋ መልሰህ ስጥ፤ እርሱ ነቢይ ስለ ሆነ እንዳትሞት ይጸልይልሃል፤ እርስዋን መልሰህ ባትሰጥ ግን እንደምትሞት ዕወቅ፤ አንተ ብቻ ሳትሆን ሕዝብህም በሙሉ ታልቃላችሁ።”
ማቴዎስ 10:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ያገኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቅን ዋጋ ያገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይቀበላል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቅን ዋጋ ይቀበላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። |
አሁን ግን ሴቲቱን ለባልዋ መልሰህ ስጥ፤ እርሱ ነቢይ ስለ ሆነ እንዳትሞት ይጸልይልሃል፤ እርስዋን መልሰህ ባትሰጥ ግን እንደምትሞት ዕወቅ፤ አንተ ብቻ ሳትሆን ሕዝብህም በሙሉ ታልቃላችሁ።”
እነርሱም ‘ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይም ተጠምተህ፥ እንግዳ ሆነህ ወይንም ታርዘህ፥ ታመህ ወይም ታስረህ መቼ አየንህና ሳንረዳህ ቀረን?’ ሲሉ ይመልሱለታል።
ንጉሡም ‘በእውነት እላችኋለሁ፤ ከእነዚህ ከወንድሞቼ አነስተኛ ለሆነው ለአንዱ እንኳ ያላደረጋችሁት ሁሉ ለእኔ እንዳላደረጋችሁት ነው’ ይላቸዋል።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ሰዎች ይዩልን ብላችሁ መልካም ሥራችሁን በሰዎች ፊት ከማድረግ ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ ግን፥ በሰማይ አባታችሁ ዘንድ ምንም ዋጋ አታገኙም።
አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ ክፍልህ ገብተህ፥ በርህን ዝጋና በስውር ወዳለው ወደማይታይ አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተሠራውን የሚያይ አባትህም የመልካም ሥራህን ዋጋ ይከፍልሃል።
እርስዋና በቤትዋ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ፥ “በጌታ የማምን መሆኔን ካረጋገጣችሁልኝ ወደ ቤቴ መጥታችሁ ተቀመጡ” ስትል አጥብቃ ለመነችን።
እኔንና በዚህ ያለውን መላ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስተናግደው ጋይዮስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ የከተማይቱ በጅሮንድ የሆነው ኤራስጦስ፥ ወንድማችንም ቋርጦስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። [
የወንጌልን ቃል ያለ ግዴታ በፈቃዴ ባበሥር የድካም ዋጋ ይኖረኛል፤ በግዴታ ባደርገው ግን በዐደራ የተሰጠኝን ኀላፊነት ፈጸምኩ እንጂ ሌላ ያደረግኹት ነገር አለ ማለት አይደለም።