ማርቆስ 6:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡ ሳያምኑ በመቅረታቸው እጅግ ተገረመ፤ ከዚህም በኋላ ኢየሱስ በየመንደሩ እየተዘዋወረ ያስተምር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባለማመናቸውም ተደነቀ። ከዚያም ኢየሱስ በየመንደሩ እየተዘዋወረ ያስተምር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባለማመናቸውም ተደነቀ። ከዚህም በኋላ ኢየሱስ በየመንደሩ እየተዘዋወረ ያስተምር ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ አለማመናቸውም ተደነቀ። በመንደሮችም እያስተማረ ይዞር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ አለማመናቸውም ተደነቀ። በመንደሮችም እያስተማረ ይዞር ነበር። |
ሐሰተኞች አማልክት ቢሆኑም እንኳ አማልክቱን የሚቀያይር ሕዝብ የለም፤ ሕዝቤ ግን ክብር ያጐናጸፍኳቸውን እኔን አምላካቸውን ምንም ሊያደርጉላቸው በማይችሉ ከንቱ አማልክት ለውጠውኛል።”
ኢየሱስም በምኲራቦቻቸው እያስተማረና የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል እየሰበከ፥ በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የተያዙትንም ሰዎች እየፈወሰ በገሊላ ምድር ሁሉ ይዘዋወር ነበር።
ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ ተደነቀ፤ ይከተሉት የነበሩትን ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “በእውነት እላችኋለሁ፤ ይህን የሚያኽል ትልቅ እምነት ያለው አንድም ሰው በእስራኤል ስንኳ አላገኘሁም።
ኢየሱስም በምኲራቦቻቸው እያስተማረ፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከ፥ ሕዝቡን ከበሽታና ከደዌ ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተሞችና በመንደሮች ሁሉ ይዘዋወር ነበር።
ኢየሱስ ከዚያ ተነሥቶ፥ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ይሁዳ ምድር ሄደ። እጅግ ብዙ ሰዎችም እንደገና ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ እርሱም እንደ ልማዱ ያስተምራቸው ነበር።
“ደግሞም እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ እንደ ቀባውና ኀይልም እንደ ሰጠው ታውቃላችሁ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ እርሱን መልካም ነገርን እያደረገና በዲያብሎስ የተያዙትን ሁሉ እየፈወሰ ተዘዋወረ።