ማርቆስ 5:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤ ከሥቃይሽም ተፈወሺ፤” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ልጄ ሆይ፤ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤ ከሥቃይሽም ዕረፊ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤ ከሥቃይሽም ተፈወሺ” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም “ልጄ ሆይ! እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤ ከሥቃይሽም ተፈወሽ፤” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ ከሥቃይሽም ተፈወሽ አላት። |
“ቤቱ እንደገና ታድሶ ከተለሰነ በኋላ ካህኑ መጥቶ በሚመለከትበት ጊዜ ሻጋታው የመስፋፋት ምልክት የማያሳይ ሆኖ ከተገኘ ግን የሻጋታው ምልክት ጨርሶ ስለ ጠፋ ያ ቤት ንጹሕ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ።
በዚያም ሰዎች በአልጋ ላይ የተኛ አንድ ሽባ ይዘው ወደ እርሱ መጡ። እርሱም እምነታቸውን አይቶ፥ ሽባውን፥ “ልጄ ሆይ! አይዞህ፤ ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው።
ይህ ሰው ጳውሎስ በሚናገርበት ጊዜ ተቀምጦ ያዳምጥ ነበር፤ ጳውሎስ ሰውየውን ትኲር ብሎ ተመለከተና ለመዳን የሚያበቃው እምነት እንዳለው ባየ ጊዜ፥
ከዚህ በኋላ ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “በሰላም ሂድ፤ እኔና አንተ በዘሬና በዘርህ መካከል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ይሁን ብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናል።” ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።