ከዚህ በኋላ ሎጥ ሴቶች ልጆቹን ወዳጩአቸው ሰዎች ቤት ሄደና “ቶሎ ብላችሁ ከዚህ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህን ስፍራ ሊደመስሰው ነው” አላቸው፤ እነርሱ ግን የሚቀልድ መስሎአቸው ቸል አሉ።
ማርቆስ 4:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃሉ በተዘራ ጊዜ በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ቃሉን በሰሙ ጊዜ ወዲያውኑ ሰይጣን መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል የሚወስድባቸውን ሰዎች ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዳንድ ሰዎች በመንገድ ላይ የወደቀውን ዘር ይመስላሉ፤ ቃሉን በሚሰሙበት ጊዜ ሰይጣን ወዲያውኑ መጥቶ በውስጣቸው የተዘራውን ቃል ይወስደዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃሉ በተዘራ ጊዜ በመንገድ ዳር የነበሩት፦ እነርሱ በሰሙት ጊዜ ሰይጣን ወዲያው መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል የሚወስድባቸው ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰሙት ጊዜም ሰይጣን ወዲያው መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል ይወስዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰሙት ጊዜም ሰይጣን ወዲያው መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል ይወስዳል። |
ከዚህ በኋላ ሎጥ ሴቶች ልጆቹን ወዳጩአቸው ሰዎች ቤት ሄደና “ቶሎ ብላችሁ ከዚህ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህን ስፍራ ሊደመስሰው ነው” አላቸው፤ እነርሱ ግን የሚቀልድ መስሎአቸው ቸል አሉ።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሊቀ ካህናቱን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ በራእይ አሳየኝ፤ ሰይጣንም ኢያሱን ለመክሰስ በስተቀኙ ቆሞ ነበር።
በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር የሚያመለክተው፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት ቃል ሰምቶ የማያስተውለውን ሰው ነው፤ ወዲያውኑ ሰይጣን መጥቶ በልቡ የተዘራውን ቃል ይወስድበታል፤
በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ቃሉን ለጊዜው የሚሰሙትን ሰዎች ነው፤ ነገር ግን እነርሱ አምነው እንዳይድኑ ዲያብሎስ መጥቶ ቃሉን ከልባቸው ይወስዳል።
ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፦ “ሐናንያ ሆይ! በመንፈስ ቅዱስ ላይ እንድትዋሽና ከመሬቱም ሽያጭ ከፊሉን እንድታስቀር ያደረገህ ሰይጣን ስለምን ወደ ልብህ ገባ?
ታላቁም ዘንዶ ወደታች ተጣለ፤ እርሱ መላውን ዓለም የሚያስተው ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የቀድሞው እባብ ነው። እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ የእርሱም መላእክት ከእርሱ ጋር አብረው ተጣሉ።
ያሳታቸው ዲያብሎስ፥ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት በዲን በሚቃጠል እሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ፤ በዚያም ሌሊትና ቀን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሠቃያሉ።