እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ድምፅህን ሳትቈጥብ ጩኽ! ድምፅህ እንደ እምቢልታ ከፍ ይበል! ለሕዝቤ ለእስራኤል ዐመፃቸውንና ኃጢአታቸውን ንገራቸው።
ማርቆስ 3:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቦአኔርጌስ ወይም የነጐድጓድ ልጆች ብሎ የሠየማቸው፥ የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቦአኔርጌስ ይኸውም፣ “የነጐድጓድ ልጆች” ብሎ የጠራው የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብና ወንድሙ ዮሐንስ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቦአኔርጌስ፥ ማለትም የነጐድጓድ ልጆች ብሎ የሰየማቸው የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና የያዕቆብ ወንድም ዮሐንስን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዘብዴዎስንም ልጅ ያዕቆብን የያዕቆብንም ወንድም ዮሐንስን ቦአኔርጌስ ብሎ ሰየማቸው፤ የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዘብዴዎስንም ልጅ ያዕቆብን የያዕቆብንም ወንድም ዮሐንስን ቦአኔርጌስ ብሎ ሰየማቸው፥ የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፤ |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ድምፅህን ሳትቈጥብ ጩኽ! ድምፅህ እንደ እምቢልታ ከፍ ይበል! ለሕዝቤ ለእስራኤል ዐመፃቸውንና ኃጢአታቸውን ንገራቸው።
ከዚያም እልፍ ብሎ፥ የዘብዴዎስ ልጆች የሆኑትን ሌሎች ሁለት ወንድማማች ያዕቆብንና ዮሐንስን አየ። እነርሱም ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በጀልባ ላይ ሆነው መረባቸውን ሲጠግኑ ሳለ ጠራቸው።
ደቀ መዛሙርቱ ያዕቆብና ዮሐንስ ይህን ባዩ ጊዜ፥ “ጌታ ሆይ! ከሰማይ እሳት ወርዶ እነዚህን ሰዎች ያቃጥላቸው ዘንድ እንድናዝዝ ትፈቅዳለህን?” አሉት።
የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነው፤ ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ ስለታም ነው፤ ነፍስንና መንፈስን፥ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ የሚቈራርጥ ነው፤ በልብ ውስጥ የተሰወረውንም ሐሳብና ምኞት መርምሮ የሚፈርድ ነው።
ከዚህ በኋላ “ስለ ብዙ ወገኖች፥ ሕዝቦች፥ ልዩ ልዩ ቋንቋ ስለሚናገሩ ሰዎችና ስለ ነገሥታት እንደ ገና ትንቢት መናገር አለብህ” ተብሎ ተነገረኝ።