ማርቆስ 15:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠዋት በማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎች፥ ከሕግ መምህራን፥ ከሸንጎውም አባሎች ሁሉ ጋር ተማከሩ፤ ከዚያም በኋላ ኢየሱስን አስረው ወሰዱትና ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወዲያውም በማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎች፣ ከጸሐፍትና ከመላው የሸንጎ አባላት ጋራ ከተማከሩ በኋላ፣ ኢየሱስን አስረው ወሰዱት፤ ለጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠዋት በማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎች፥ ከጸሓፍትና ከመላው የሸንጎ አባላት ጋር ወዲያው ከተማከሩ በኋላ ኢየሱስን አስረው ወሰዱት፤ ለጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዲያውም ማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎችና ከጻፎች ከሸንጎውም ሁሉ ጋር ከተማከሩ በኋላ፥ ኢየሱስን አሳስረው ወሰዱትና ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወዲያውም ማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎችና ከጻፎች ከሸንጎውም ሁሉ ጋር ከተማከሩ በኋላ፥ ኢየሱስን አሳስረው ወሰዱትና ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት። |
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በወንድሙ ላይ የሚቈጣ ሁሉ ይፈረድበታል፤ ደግሞም ወንድሙን፥ ‘አንተ የማትረባ!’ ብሎ የሚሳደብ በሸንጎ ይፈረድበታል፤ ‘ደደብ!’ ብሎ የሚሳደብ ሁሉ በገሃነመ እሳት ይፈረድበታል።
የአባቶቻችን የአብርሃም፥ የይስሐቅና፥ የያዕቆብ አምላክ ልጁን ኢየሱስን አከበረው፤ እናንተ ግን እርሱን በጲላጦስ ፊት አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ጲላጦስም ሊለቀው ቢፈልግ እንኳ ‘አንፈልግም’ አላችሁ።